ሰሎሞንም፦ “እርሱ አካሄዱን ያሳመረ እንደሆነ ከእርሱ አንዲት ጠጉር እንኳ በምድር ላይ አትወድቅም፥ ነገር ግን ክፋት የተገኘበት እንደሆነ ይሞታል” አለ።
ሐዋርያት ሥራ 27:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ምግብ ትበሉ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤ ይህ ለደኅንነታችሁ ይሆናልና፤ ከእናንተ ከአንዱ የራስ ጠጉር እንኳ አትጠፋምና።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ፣ ለደኅንነታችሁ አሁን እህል እንድትቀምሱ እለምናችኋላሁ፤ ከእናንተ መካከል ከራሱ ጠጕር አንዲት እንኳ የሚነካበት ማንም የለምና።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እህል እንድትቀምሱ እለምናችኋለሁ። ይህም ብርታት ይሰጣችኋል፤ ከቶ ምንም ዐይነት ጒዳት አይደርስባችሁም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም እሺ በሉኝና ምግብ ብሉ፤ ራሳችሁንም አድኑ፥ ከእናንተ ከአንዱ የራስ ጠጕር እንኳ አትጠፋምና።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰለዚህ ምግብ ትበሉ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤ ይህ ለደኅንነታችሁ ይሆናልና፤ ከእናንተ ከአንዱ የራስ ጠጕር እንኳ አትጠፋምና።” |
ሰሎሞንም፦ “እርሱ አካሄዱን ያሳመረ እንደሆነ ከእርሱ አንዲት ጠጉር እንኳ በምድር ላይ አትወድቅም፥ ነገር ግን ክፋት የተገኘበት እንደሆነ ይሞታል” አለ።
ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን ወደ እርሱ ጠርቶ “ለሕዝቡ አዝንላቸዋለሁ፥ ምክንያቱም ከእኔ ጋር እስካሁን ሦስት ቀን ውለዋል የሚበሉት ግን የላቸውም፤ በመንገድ ላይ እንዳይዝሉ ጦማቸውን ላሰናብታቸው አልፈልግም” አላቸው።
ቀንም ሲነጋ ጳውሎስ ምግብ ይበሉ ዘንድ ሁሉን ይለምን ነበር፤ እንዲህም አላቸው “እየጠበቃችሁ ምንም ሳትቀበሉ ጦማችሁን ከሰነበታችሁ ዛሬ ዐሥራ አራተኛ ቀናችሁ ነው።
ሕዝቡ ግን ሳኦልን፥ “ለእስራኤል ይህን ታላቅ ድል ያስገኘ ዮናታን መሞት ይገባዋልን? ይህ አይሆንም! ዛሬ ይህን ያደረገው በእግዚአብሔር ርዳታ ስለ ሆነ፥ ሕያው ጌታን! ከራስ ጠጉሩ አንዲቱ እንኳ መሬት ላይ አትወድቅም” አሉት። ስለዚህ ሰዎቹ ዮናታንን ታደጉት፤ እርሱም ከመሞት ዳነ።