ማቴዎስ 15:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)32 ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን ወደ እርሱ ጠርቶ “ለሕዝቡ አዝንላቸዋለሁ፥ ምክንያቱም ከእኔ ጋር እስካሁን ሦስት ቀን ውለዋል የሚበሉት ግን የላቸውም፤ በመንገድ ላይ እንዳይዝሉ ጦማቸውን ላሰናብታቸው አልፈልግም” አላቸው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም32 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ራሱ ጠርቶ፣ “ሕዝቡ ከእኔ ጋራ ሦስት ቀን ስለ ሆናቸውና የሚበሉት ስለሌላቸው ለእነዚህ ሰዎች ዐዝንላቸዋለሁ፤ በመንገድ ላይ በራብ ዝለው እንዳይወድቁ ጦማቸውን ልሰድዳቸው አልፈቅድም” አለ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም32 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ፥ እንዲህ አላቸው፦ “ሰዎቹ ከእኔ ጋር ሦስት ቀናቸው ስለ ሆነና የሚበሉት ስለሌላቸው እራራላቸዋለሁ፤ ሲሄዱ በመንገድ ዝለው እንዳይወድቁ ምንም ሳይመገቡ ላሰናብታቸው አልፈቅድም።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)32 ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ “ሕዝቡ ከእኔ ጋር እስካሁን ሦስት ቀን ውለዋልና የሚበሉት ስለሌላቸው አዝንላቸዋለሁ፤ በመንገድም እንዳይዝሉ ጦማቸውን ላሰናብታቸው አልወድም፤” አላቸው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)32 ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ፦ ሕዝቡ ከእኔ ጋር እስካሁን ሦስት ቀን ውለዋልና የሚበሉት ስለ ሌላቸው አዝንላቸዋለሁ፤ በመንገድም እንዳይዝሉ ጦማቸውን ላሰናብታቸው አልወድም አላቸው። Ver Capítulo |