በብንያምም በር በነበረ ጊዜ የሐናንያ ልጅ የሰሌምያ ልጅ የሪያ የተባለ የዘበኞች አለቃ በዚያ ነበረ፤ እርሱም ነቢዩን ኤርምያስን፦ “ወደ ከለዳውያን ልትኰበልል ነው” ብሎ ያዘው።
ሐዋርያት ሥራ 24:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ ሰው በሽታ ሆኖ በዓለም ባሉት አይሁድ ሁሉ ሁከት ሲያስነሣ፥ የመናፍቃን የናዝራውያን ወገን መሪ ሆኖ አግኝተነዋልና፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ይህ ሰው፣ በዓለም ባሉት አይሁድ ሁሉ መካከል በሽታ ሆኖ ሁከት የሚያስነሣ፣ ደግሞም የናዝራውያን ወገን ቀንደኛ መሪ ሆኖ አግኝተነዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ ሰው መጥፎ በሽታ ሆኖብናል፤ በዓለም ባሉት አይሁድ ሁሉ ላይ ሁከት ያስነሣል፤ ናዝራውያን ለሚባሉት መሪያቸው ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህን ሰው ሲሳደብና ወንጀል ሲሠራ፥ አይሁድንም ሁሉ በየሀገሩ ሲያውክ፥ ናዝራውያን የተባሉት ወገኖች የሚያስተምሩትንም ክህደት ሲያስተምር አግኝተነዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ ሰው በሽታ ሆኖ በዓለም ባሉት አይሁድ ሁሉ ሁከት ሲያስነሣ፥ የመናፍቃን የናዝራውያን ወገን መሪ ሆኖ አግኝተነዋልና፤ |
በብንያምም በር በነበረ ጊዜ የሐናንያ ልጅ የሰሌምያ ልጅ የሪያ የተባለ የዘበኞች አለቃ በዚያ ነበረ፤ እርሱም ነቢዩን ኤርምያስን፦ “ወደ ከለዳውያን ልትኰበልል ነው” ብሎ ያዘው።
አለቆቹም ንጉሡን፦ “ይህን የመሰለውን ቃላት እየነገራቸው የሕዝቡን ሁሉ እጅ በዚህችም ከተማ የቀሩትን የወታደሮቹን እጅ እያደከመ ነውና ይህ ሰው እንዲገደል እንለምንሃለን፤ ይህ ሰው ክፋትን እንጂ ለዚህ ሕዝብ ሰላምን አይመኝለትምና” አሉት።
የቤቴልም ካህን አሜስያስ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዮርብዓም እንዲህ ብሎ ላከ፦ “አሞጽ በእስራኤል ቤት መካከል አሢሮብሃል፤ ምድሪቱም ቃሉን ሁሉ ልትሸከም አትችልም።
ደቀመዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባርያም እንደ ጌታው ከሆነ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔልዜቡል ካሉት፥ ቤተሰቦቹንማ እንዴት ከዚህ የበለጠ አይሉአቸው?
“ይህ ሕዝባችንን ሲያስት ለቄሣርም ግብር እንዳይሰጥ ሲከለክል፥ ደግሞም ‘እኔ ክርስቶስ ንጉሥ ነኝ፤’ ሲል አገኘነው” ብለው ይከሱት ጀመር።
ሁከት በመፍጠርና ሰውን በመግደል ምክንያት ታስሮ የነበረውን በጥያቄአቸው መሠረት አስፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን እንደ ፈቃዳቸው አሳልፎ ሰጠው።
እስከዚህም ቃል ድረስ ይሰሙት ነበር፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው፥ “እነደዚህ ያለውን ሰው ከምድር አስወግደው፤ በሕይወት ይኖር ዘንድ አይገባውምና፤” አሉ።
ነገር ግን ይህን እመሰክርልሃለሁ፤ በሕጉ ያለውን በነቢያትም የተጻፉትን ሁሉ አምኜ የአባቶቼን አምላክ እነርሱ ኑፋቄ ብለው እንደሚጠሩት መንገድ አመልካለሁ፤
ሊመሰክሩ ይወዱ እንደሆነ፥ በአምልኮአችን ከሁሉ ይልቅ ሕግን በመጠንቀቅ እንደሚተጋ ወገን ፈሪሳዊ ሆኜ እንደኖርሁ ከጥንት ጀምረው አውቀውኛልና።