Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 37:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በብንያምም በር በነበረ ጊዜ የሐናንያ ልጅ የሰሌምያ ልጅ የሪያ የተባለ የዘበኞች አለቃ በዚያ ነበረ፤ እርሱም ነቢዩን ኤርምያስን፦ “ወደ ከለዳውያን ልትኰበልል ነው” ብሎ ያዘው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ነገር ግን ወደ ብንያም በር ሲደርስ፣ የዘበኞች አለቃ የነበረው የሐናንያ ልጅ የሰሌምያ ልጅ የሪያ፣ ነቢዩ ኤርምያስን፣ “ከድተህ ወደ ባቢሎናውያን ልትሄድ ነው!” በማለት ያዘው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ነገር ግን ከብንያም ቅጽር በር እንደ ደረስኩ የዘብ ጠባቂዎች አለቃ የሆነው ስሙ ዪሪያ ተብሎ የሚጠራ የሐናንያ የልጅ ልጅ የሆነው የሼሌምያ ልጅ “ከድተህ ወደ ባቢሎናውያን ልትሄድ ነው!” ብሎ አስቆመኝ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በብ​ን​ያ​ምም በር በነ​በረ ጊዜ የሐ​ና​ንያ ልጅ የሰ​ሌ​ምያ ልጅ ሳሩያ የተ​ባለ በር ጠባቂ በዚያ ነበረ፤ እር​ሱም፥ “ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን መኰ​ብ​ለ​ልህ ነው” ብሎ ነቢ​ዩን ኤር​ም​ያ​ስን ያዘው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በብንያምም በር በነበረ ጊዜ የሐናንያ ልጅ የሰሌምያ ልጅ የሪያ የተባለ የዘበኞች አለቃ በዚያ ነበረ፥ እርሱም፦ ወደ ከለዳውያን መኰብለልህ ነው ብሎ ነቢዩን ኤርምያስን ያዘው።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 37:13
20 Referencias Cruzadas  

ምድር ሁሉ ከጌባ ጀምሮ በኢየሩሳሌምም ደቡብ በኩል እስካለችው እስከ ሬሞን ድረስ ተለውጣ፥ እንደ ዓረባ ትሆናለች፤ እርሷም ከፍ ከፍ ትላለች፥ ከብንያምም በር ጀምሮ እስከ ፊተኛው የበሯ ስፍራ እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ፥ ከሐናንኤልም ግንብ ጀምሮ እስከ ንጉሡ መጥመቂያ ድረስ በስፍራዋ ትኖራለች።


በንጉሡም ቤት የነበረው ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ አቤሜሌክ ኤርምያስን በጉድጓዱ ውስጥ እንዳኖሩት ሰማ። ንጉሡም በብንያም በር ተቀምጦ ነበር።


አሁንም ስለሚከሱኝ ያስረዱህ ዘንድ አይችሉም።


በዚያን ጊዜ “በሙሴ ላይ በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር ሰምተነዋል፤” የሚሉ ሰዎችን አስነሡ።


“ይህ ሕዝባችንን ሲያስት ለቄሣርም ግብር እንዳይሰጥ ሲከለክል፥ ደግሞም ‘እኔ ክርስቶስ ንጉሥ ነኝ፤’ ሲል አገኘነው” ብለው ይከሱት ጀመር።


ኤርምያስም ለሕዝቡ ሁሉ የተናገረውን ቃላት የማታን ልጅ ስፋጥያስ፥ የጳስኮርም ልጅ ጎዶልያስ፥ የሰሌምያም ልጅ ዮካል፥ የመልክያም ልጅ ጳስኮር ሰሙ።


በዚህች ከተማ ውስጥ የሚቀር በሰይፍና በራብ በቸነፈርም ይሞታል፤ ወጥቶ ወደ ከበቡአችሁ ወደ ከለዳውያን የሚገባ ግን በሕይወት ይኖራል፥ እርሱም በምርኮ ነፍሱን ያድናል።


የብዙ ሰዎችን የክፋት ሹክሹክታ ሰምቻለሁ፥ ማስፈራራትም ከብቦኛል። መውደቄን የሚጠብቁ የሰላሜ ሰዎች ሁሉ፦ “ምናልባት ይታለል እንደሆነ፥ እናሸንፈውም እንደሆነ፥ እርሱንም እንበቀል እንደሆነ፥ ክሰሱት እኛም እንከስሰዋለን” ይላሉ።


እነርሱም፦ “ሕግ ከካህን፥ ምክርም ከጠቢብ፥ ቃልም ከነቢይ አይጠፋምና ኑ፥ በኤርምያስ ላይ ሤራን እናሢር። ኑ፥ በአንደበት እንምታው፥ ቃላቱንም ሁሉ አናድምጥ” አሉ።


በክብርና በውርደት፥ በመመስገንና በመሰደብ ኖረናል። አሳቾች ስንባል እውነተኞች ነን፤


የቤቴልም ካህን አሜስያስ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዮርብዓም እንዲህ ብሎ ላከ፦ “አሞጽ በእስራኤል ቤት መካከል አሢሮብሃል፤ ምድሪቱም ቃሉን ሁሉ ልትሸከም አትችልም።


አለቆቹም ንጉሡን፦ “ይህን የመሰለውን ቃላት እየነገራቸው የሕዝቡን ሁሉ እጅ በዚህችም ከተማ የቀሩትን የወታደሮቹን እጅ እያደከመ ነውና ይህ ሰው እንዲገደል እንለምንሃለን፤ ይህ ሰው ክፋትን እንጂ ለዚህ ሕዝብ ሰላምን አይመኝለትምና” አሉት።


ወደ ንጉሡ ቤት ወደ ጸሐፊው ጓዳ ወረደ፤ እነሆም፥ አለቆች ሁሉ፥ ጸሐፊው ኤሊሳማ፥ የሸማያ ልጅ ድላያ፥ የዓክቦር ልጅ ኤልናታን፥ የሳፋን ልጅ ገማርያ፥ የሐናንያ ልጅ ሴዴቅያስ አለቆቹም ሁሉ በዚያ ተቀምጠው ነበር።


የእስራኤልም አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እንዲያገለግሉት የብረትን ቀንበር በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ አንገት ላይ አድርጌአለሁ፤ እነርሱም ያገለግሉታል፥ ሌላው ቀርቶ የምድረ በዳ አራዊትን ሰጥቼዋለሁ።’ ”


አሁንም እነዚህን ምድሮች ሁሉ ለባርያዬ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ ሰጥቻለሁ፤ እንዲያገለግሉትም የምድረ በዳን አራዊት ደግሞ ሰጥቼዋለሁ።


ጳስኮርም ነቢዩን ኤርምያስን መታው፥ በጌታም ቤት በነበረው በላይኛው በብንያም በር ባለው በመንቈር ውስጥ አሠረው።


ጻዴ። በአደባባያችን እንዳንሄድ ፍለጋችንን ተከተሉ፥ ፍጻሜያችን ቀርቦአል፥ ዕድሜያችን አልቆአል፥ ፍጻሜያችን ደርሶአል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios