ሐዋርያት ሥራ 23:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታላቅ ጩኸትም ሆነ፤ ከፈሪሳውያንም ወገን የሆኑት ጻፎች ተነሥተው “በዚህ ሰው ላይ ምንም ክፉ ነገር አላገኘንበትም፤ መንፈስ ወይስ መልአክ ተናግሮት ይሆን?” ብለው ተከራከሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታላቅ ሁከትም ሆነ፤ ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑ አንዳንድ የኦሪት ሕግ መምህራንም ተነሥተው፣ “በዚህ ሰው ላይ ምንም ጥፋት አላገኘንበትም፤ መንፈስ ወይም መልአክ ተናግሮትስ እንደ ሆነ ምን ይታወቃል?” በማለት አጥብቀው ተከራከሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ ታላቅ ሁካታ ሆነ፤ ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑ አንዳንድ የሕግ መምህራንም ተነሡና “እኛ በዚህ ሰው ላይ ምንም ክፉ ነገር አላገኘንበትም፤ መንፈስ ወይም መልአክ ተናግሮት ይሆናል፤ እኛ ምን እናውቃለን?” በማለት ተከራከሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታላቅ ውካታም ሆነ፤ ከፈሪሳውያንም ወገን የሆኑ ጸሐፍት ተነሥተው ይጣሉና ይከራከሩ ጀመሩ፤ “በዚህ ሰው ላይ ያገኘነው ክፉ ነገር የለም፤ መንፈስ ወይም መልአክ ተናግሮት እንደ ሆነ እንጃ፥ ከእግዚአብሔር ጋር አንጣላ” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታላቅ ጩኸትም ሆነ፥ ከፈሪሳውያንም ወገን የሆኑት ጻፎች ተነሥተው፦ በዚህ ሰው ላይ ምንም ክፉ ነገር አላገኘንበትም፤ መንፈስ ወይስ መልአክ ተናግሮት ይሆን? ብለው ተከራከሩ። |
ጸሐፍት ፈሪሳውያንም ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር ሲበላ አይተው ለደቀ መዛሙርቱ “ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር የሚበላና የሚጠጣ ስለ ምንድነው?” አሉ።
እንግዲህ እግዚአብሔር በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላመነው ለእኛ ደግሞ እንደ ሰጠን ያን ስጦታ ለእነርሱ ከሰጠ፥ እግዚአብሔርን ለመከላከል እችል ዘንድ እኔ ማን ነበርሁ?”
ሳሙኤልም፥ “በእጄ ምንም እንዳላገኛችሁ ጌታና እርሱ የቀባው ዛሬ በእናንተ ላይ ምስክሮች ናቸው” አላቸው። እነርሱም፥ “እርሱ ምስክር ነው” አሉ።