ሐዋርያት ሥራ 22:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሻለቃው ወደ ሰፈሩ እንዲያገቡት አዘዘ፤ እንደዚህም የጮኹበትን ምክንያት ያውቅ ዘንድ “እየገረፋችሁ መርምሩት፤” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጦር አዛዡ ጳውሎስን ወደ ጦር ሰፈር እንዲያስገቡትና ሕዝቡ ለምን እንዲህ እንደሚጮኹበት እየተገረፈ እንዲመረመር ትእዛዝ ሰጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አዛዡ ይህን ባየ ጊዜ ጳውሎስን ወደ ወታደሮች ሰፈር እንዲያስገቡት አዘዘ፤ ሕዝቡ በእርሱ ላይ ስለምን ይህን ያኽል እንደሚጮኹ ለማወቅም እየተገረፈ እንዲመረመር አዘዘ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሻለቃው የሚጮሁበት ስለ ምን እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ ወደ ወታደሮች ሰፈር እንዲያገቡትና እየገረፉ የሠራውን እንዲመረምሩት አዘዘ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሻለቃው ወደ ሰፈሩ እንዲያገቡት አዘዘ፥ እንደዚህም የጮኹበትን ምክንያት ያውቅ ዘንድ፦ እየገረፋችሁ መርምሩት አላቸው። |
ጳውሎስ ግን “እኛ የሮሜ ሰዎች ስንሆን ያለ ፍርድ በሕዝብ ፊት ደብድበው በወኅኒ ጣሉን፤ አሁንም በስውር ይጥሉናልን? አይሆንም፤ ራሳቸው ግን መጥተው ያውጡን፤” አላቸው።
ሕዝቡም እኩሌቶቹ እንዲህ እኩሌቶቹም እንዲያ እያሉ ይጮኹ ነበር፤ ስለ ጫጫታውም እርግጡን ማወቅ ባልተቻለ ጊዜ፥ ወደ ወታደሮች ሰፈር ይወስዱት ዘንድ አዘዘ።
ወደ ሰፈርም ሊያገቡት በቀረቡ ጊዜ፥ ጳውሎስ የሻለቃውን “አንድ ነገር ብነግርህ ትፈቅዳለህን?” አለው። እርሱም “የግሪክ ቋንቋ ታውቃለህን?
ብዙ ጥልም በሆነ ጊዜ የሻለቃው ጳውሎስን እንዳይገነጣጥሉት ፈርቶ ጭፍሮቹ ወርደው ከመካከላቸው እንዲነጥቁት ወደ ሰፈሩም እንዲያገቡት አዘዘ።