ሙሴም እጅግ ተቈጣ፥ ጌታንም እንዲህ አለው፦ “ወደ ቁርባናቸው አትመልከት፤ እኔ ከእነርሱ አንድ አህያ እንኳ አልወሰድሁም፥ ከእነርሱም አንድ ሰው አልበደልሁም።”
ሐዋርያት ሥራ 20:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከማንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የማንንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ የማንንም ብር፥ ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወርቅም ቢሆን፥ ብርም ቢሆን፥ ልብስም ቢሆን ከእናንተ ከአንዱ ስንኳ አልተመኘሁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከማንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም፤ |
ሙሴም እጅግ ተቈጣ፥ ጌታንም እንዲህ አለው፦ “ወደ ቁርባናቸው አትመልከት፤ እኔ ከእነርሱ አንድ አህያ እንኳ አልወሰድሁም፥ ከእነርሱም አንድ ሰው አልበደልሁም።”
ሌሎች በእናንተ ላይ ይህን የመካፈል መብት ያላቸው ከሆነ፥ እኛማ ይልቁን አይኖረንም? በዚህ መብት ግን አልተጠቀምንም፥ ነገር ግን የክርስቶስን ወንጌል በምንም እንዳንከለክል በሁሉ እንታገሣለን እንጂ።
እኔ ግን ከእነዚህ በአንዱም ምንም አልተጠቀምሁም። እንዲህ እንዲሆንልኝ ይህን አልጽፍም፤ ማንም ትምክህቴን ከንቱ ከሚያደርግብኝ ሞት ይሻለኛል።
ከእናንተም ጋር እያለሁ በሚጎድለኝ ጊዜ፥ ከመቄዶንያ የመጡት ወንድሞች የጎደለኝን በሙሉ ስላሟሉልኝ፥ በማንም ላይ ሸክም አልሆንኩም፤ በማንኛውም መንገድ በእናንተ ላይ ሸክም እንዳልሆን ተጠንቅቄአለሁ፤ እጠነቀቅማለሁ።
ኀላፊነት የተሰጣችሁን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ ይህም በግድ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ፍላጎት በፈቃደኝነት፥ ለጥቅም በመስገብገብ ሳይሆን በጽኑ ፍላጎት ይሁን፤