እነርሱም የመጣላቸውን ኰርማ ወስደው ለመሥዋዕት አዘጋጅተው እስከ እኩለ ቀን ድረስ ወደ ባዓል ጸለዩ። “ባዓል ሆይ! እባክህ ስማን!” እያሉም ጮኹ። በሠሩትም መሠዊያ እየዘለሉ ዞሩ፤ ነገር ግን ምንም መልስ አላገኙም።
ሐዋርያት ሥራ 19:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አይሁዳዊ ግን እንደሆነ ባወቁ ጊዜ፥ ሁሉ በአንድ ድምፅ “የኤፌሶን አርጤምስ ታላቅ ናት!” እያሉ ሁለት ሰዓት ያህል ጮኹ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን እርሱ አይሁዳዊ መሆኑን ባወቁ ጊዜ ሁሉም በአንድ ድምፅ፣ “የኤፌሶኗ አርጤምስ ታላቅ ናት!” እያሉ ሁለት ሰዓት ያህል ጮኹ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እስክንድር አይሁዳዊ መሆኑን ሰዎቹ ሁሉ ባወቁ ጊዜ “የኤፌሶን አርጤሚስ ታላቅ ናት!” እያሉ ሁለት ሰዓት ያኽል ሁሉም በአንድ ድምፅ ጮኹ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አይሁዳዊ እንደሆነም ባወቁ ጊዜ “የኤፌሶን አርጤምስ ክብርዋ ታላቅ ነው” እያሉ ሁለት ሰዓት ያህል ሁሉም በአንድ ድምፅ ጮሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አይሁዳዊ ግን እንደ ሆነ ባወቁ ጊዜ፥ ሁሉ በአንድ ድምፅ፦ የኤፌሶን አርጤምስ ታላቅ ናት እያሉ ሁለት ሰዓት ያህል ጮኹ። |
እነርሱም የመጣላቸውን ኰርማ ወስደው ለመሥዋዕት አዘጋጅተው እስከ እኩለ ቀን ድረስ ወደ ባዓል ጸለዩ። “ባዓል ሆይ! እባክህ ስማን!” እያሉም ጮኹ። በሠሩትም መሠዊያ እየዘለሉ ዞሩ፤ ነገር ግን ምንም መልስ አላገኙም።
ይህም ጳውሎስ ‘በእጅ የተሠሩቱ አማልክት አይደሉም፤’ ብሎ፥ በኤፌሶን ብቻ ሳይሆን ከጥቂት ክፍል በቀር በእስያ ሁሉ ብዙ ሕዝብን እንደ አስረዳና እንደ አሳተ አይታችኋል፤ ሰምታችሁማል።
የከተማይቱም ጸሐፊ ሕዝቡን ጸጥ አሰኝቶ እንዲህ አለ “የኤፌሶን ሰዎች ሆይ! የኤፌሶን ከተማ ለታላቂቱ አርጤምስ ከሰማይም ለወረደው ጣዖትዋ የመቅደስ ጠባቂ መሆንዋን የማያውቅ ሰው ማን ነው?
ለአውሬው ሥልጣንን ሰጥቶታልና ለዘንዶውም ሰገዱለት፤ ለአውሬውም “አውሬውን ማን ይመስለዋል? እርሱንስ ሊዋጋ ማን ይችላል?” እያሉ ሰገዱለት።