1 ነገሥት 18:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 እነርሱም የመጣላቸውን ኰርማ ወስደው ለመሥዋዕት አዘጋጅተው እስከ እኩለ ቀን ድረስ ወደ ባዓል ጸለዩ። “ባዓል ሆይ! እባክህ ስማን!” እያሉም ጮኹ። በሠሩትም መሠዊያ እየዘለሉ ዞሩ፤ ነገር ግን ምንም መልስ አላገኙም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም26 ስለዚህ የተሰጣቸውን ወይፈን ወስደው አዘጋጁት። ከዚያም ከጧት እስከ እኩለ ቀን የበኣልን ስም ጠሩ፤ “በኣል ሆይ ስማን” እያሉ ጮኹ፤ ድምፅ ግን የለም፤ የሚመልስ አልነበረም፤ በሠሩት መሠዊያ ዙሪያም እየዘለሉ ያሸበሽቡ ነበር። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 እነርሱም የመጣላቸውን ኰርማ ወስደው ለመሥዋዕት አዘጋጅተው እስከ እኩለ ቀን ድረስ ወደ ባዓል ጸለዩ። “ባዓል ሆይ! እባክህ ስማን!” እያሉም ጮኹ። በሠሩትም መሠዊያ እየዘለሉ ዞሩ፤ ነገር ግን ምንም መልስ አላገኙም። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 የተሰጣቸውን ወይፈንም ወስደው አዘጋጁ፤ ከጥዋትም እስከ ቀትር ድረስ፥ “በዓል ሆይ፥ ስማን፥” እያሉ የበዓልን ስም ጠሩ። ድምፅም አልነበረም፤ የሚመልስም አልነበረም፤ የሠሩትንም መሠዊያ እያነከሱ ይዞሩ ነበር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 ወይፈኑንም ወስደው አዘጋጁ፤ ከጥዋትም እስከ ቀትር ድረስ “በኣል ሆይ! ስማን፤” እያሉ የበኣልን ስም ጠሩ። ድምፅም አልነበረም፤ የሚመልስም አልነበረም፤ በሠሩትም መሠዊያ ዙሪያ እያነከሱ ያሸበሽቡ ነበር። Ver Capítulo |