ባነበቡትም ጊዜ ከምክሩ የተነሣ ደስ አላቸው።
ሕዝቡም ካነበቡት በኋላ አበረታታች በሆነው ቃሉ ደስ ተሠኙ።
አማኞቹም ደብዳቤውን ባነበቡ ጊዜ በሚያጽናናው መልእክት እጅግ ደስ አላቸው።
እነርሱም አንብበው እጅግ ደስ አላቸው፥ ተጽናኑም።
አንዳንዶችም ከይሁዳ ወረዱና “እንደ ሙሴ ሥርዓት ካልተገረዛችሁ ትድኑ ዘንድ አትችሉም፤” ብለው ወንድሞችን ያስተምሩ ነበር።
እንግዲህ አባቶቻችንና እኛ ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ በመጫን እግዚአብሔርን አሁን ስለምን ትፈታተናላችሁ?
እነርሱም ተሰናብተው ወደ አንጾኪያ ወረዱ፤ ሕዝቡንም ሰብስበው ደብዳቤውን ሰጡአቸው።
ይሁዳና ሲላስም ደግሞ ነቢያት ነበሩና ወንድሞችን በብዙ ቃል መክረው አጸኑአቸው።
አብያተ ክርስቲያናትም በሃይማኖት ይበረቱ ነበር፤ በቍጥር ም ዕለት ዕለት ይበዙ ነበር።
በነጻነት እንድንኖር ክርስቶስ ነጻ አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በባርነት ቀንበር እንደገና አትያዙ።
እኛ በመንፈስ እግዚአብሔርን የምናመልክ በክርስቶስ ኢየሱስም የምንመካ በሥጋም የማንታመን በእውነትም ከተገረዙት ወገን የሆንን ነንና።