ከዚህ በኋላ ኤልያቄምና ሼብና እንዲሁም ዮአሕ በኀዘን ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ቀርበው የአሦራውያን ባለ ሥልጣን የተናገረውን አስረዱት።
ሐዋርያት ሥራ 14:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐዋርያት በርናባስና ጳውሎስ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ልብሳቸውን ቀደው ወደ ሕዝቡ መካከል እየጮኹ ሮጡ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐዋርያቱ በርናባስና ጳውሎስ ይህን በሰሙ ጊዜ ልብሳቸውን ቀድደው ወደ ሕዝቡ መካከል ሮጡ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው እንዲህ አሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሐዋርያቱ ጳውሎስና በርናባስ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ በሐዘን ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ወደ ሕዝቡ ሮጡና እየጮኹ እንዲህ አሉ፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐዋርያት በርናባስና ጳውሎስም በሰሙ ጊዜ፥ ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ፈጥነውም እየጮኹ ወደ ሕዝቡ ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሐዋርያት በርናባስና ጳውሎስ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ልብሳቸውን ቀደው ወደ ሕዝቡ መካከል እየጮኹ ሮጡ፥ |
ከዚህ በኋላ ኤልያቄምና ሼብና እንዲሁም ዮአሕ በኀዘን ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ቀርበው የአሦራውያን ባለ ሥልጣን የተናገረውን አስረዱት።
የእስራኤልም ንጉሥ ደብዳቤውን ባነበበ ጊዜ በቁጣ ልብሱን ቀደደ፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ “የሶርያ ንጉሥ ይህን ሰው እንደምፈውስለት አድርጎ እንዴት ይገምታል? እኔ ሰውን ከቆዳ በሽታ እፈውስ ዘንድ የማዳንና የመግደል ሥልጣን ያለኝ እግዚአብሔር መሰልኩትን? በእርግጥ ይህ አባባል ከእኔ ጋር ጠብ መፈለጉን በግልጥ ያሳያል!” አለ።
በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህኑ ልብሱን ቀደደና እንዲህ አለ “ተሳድቦአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ምስክሮችን መያዝ ለምን ያስፈልገናል? እነሆ አሁን ስድቡን ሰምታችኋል፤