ሐዋርያት ሥራ 13:49 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታም ቃል በአገሩ ሁሉ ተስፋፋ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጌታም ቃል በአካባቢው ባለው አገር ሁሉ ተስፋፋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጌታም ቃል በዚያ አገር ሁሉ ተስፋፋ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም ቃል በሀገሩ ሁሉ ተዳረሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጌታም ቃል በአገሩ ሁሉ ተስፋፋ። |
ይህም ጳውሎስ ‘በእጅ የተሠሩቱ አማልክት አይደሉም፤’ ብሎ፥ በኤፌሶን ብቻ ሳይሆን ከጥቂት ክፍል በቀር በእስያ ሁሉ ብዙ ሕዝብን እንደ አስረዳና እንደ አሳተ አይታችኋል፤ ሰምታችሁማል።
የእግዚአብሔርም ቃል እየሰፋ ሄደ፤ በኢየሩሳሌምም የደቀ መዛሙርት ቍጥር እጅግ እየበዛ ሄደ፤ ከካህናትም ብዙ ሰዎች ለሃይማኖት የታዘዙ ሆኑ።