2 ጢሞቴዎስ 4:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤርስጦስ በቆሮንቶስ ቀረ፤ ጥሮፊሞስን ግን ታሞ በሚሊጢን ተውኩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤርስጦስ በቆሮንቶስ ቀርቷል፤ ጥሮፊሞስም ስለ ታመመ በሚሊጢን ትቼዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤራስጦስ በቆሮንቶስ ቀርቶአል፤ ጥሮፊሞስ ስለ ታመመ በሚሊጢ ትቼዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤርስጦስ በቆሮንቶስ ቀረ፤ ጥሮፊሞስን ግን ታሞ በሚሊጢን ተውሁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤርስጦስ በቆሮንቶስ ቀረ፥ ጥሮፊሞስን ግን ታሞ በሚሊጢን ተውሁት። |
በማግሥቱም ከዚያ በባሕር ተነሥተን በኪዩ ፊት ለፊት ደረስን፤ በነገውም ወደ ሳሞን ተሻገርን፤ በትሮጊሊዮም አድረን በማግሥቱ ወደ ሚሊጢን መጣን።
የሸኙትም የቤርያው ሶጳጥሮስ ከተሰሎንቄ ሰዎችም አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ የደርቤኑም ጋይዮስና ጢሞቴዎስ የእስያ ሰዎችም ቲኪቆስ ጥሮፊሞስም ነበሩ፤
እኔንና መላዋ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስተናግደው ጋዩስ ሰላምታ ያቀርብላችኋል። የከተማው ገንዘብ ያዥ ኤራስቶስ፥ ወንድማችንም ኳርቶስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።