2 ጢሞቴዎስ 2:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ መልካም ወታደር ሆነህ መከራን ተቀበል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ በጎ ወታደር ከእኛ ጋራ መከራን ተቀበል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተም የኢየሱስ ክርስቶስ መልካም ወታደር በመሆን ከእኔ ጋር መከራን ተቀበል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ ወታደር ሆነህ፥ አብረኸኝ መከራ ተቀበል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ ወታደር ሆነህ፥ አብረኸኝ መከራ ተቀበል። |
ከቶ በገዛ ገንዘቡ በወታደርነት የሚያገለግል ማን ነው? ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላ ማን ነው? ወይስ መንጋ እየጠበቀ ከመንጋው ወተት የማይጠጣ ማን ነው?
መከራ ብንቀበል፥ ስለ መጽናናታችሁና ስለ መዳናችሁ ነው፤ ብንጽናናም፥ እኛ የተቀበልነውን መከራ በመቀበል እናንተም በትዕግሥት መታገስ በመቻላችሁ፥ ስለ መጽናናታችሁ ነው።
ልጄ ጢሞቴዎስ ሆይ! አስቀድሞ ስለ አንተ የተነገረውን ትንቢት ሁሉ መሠረት በማድረግ፥ በእነርሱ መልካም ውጊያን እንድትዋጋ ይህችን ትእዛዝ በአደራ ለአንተ እሰጥሃለሁ፤
እንግዲህ ስለ ጌታችን ምስክርነት በመስጠት ወይም ስለ እርሱ በታሰርሁ በእኔ አትፈር ይልቁንም እንደ እግዚአብሔር ኃይል መጠን ስለ ወንጌል አብረኸኝ መከራን ተቀበል።
ስደቴንም፥ መከራዬንም ተከተልህ፤ በአንጾኪያና በኢቆንዮን በልስጥራንም የደረሰብኝን ነገርና የታገሥሁትን ስደት ታውቃለህ፤ ጌታ ግን ከሁሉም አዳነኝ።