አሁን ግን፥ ዘሩባቤል ሆይ፥ በርታ፥ ይላል ጌታ፤ ታላቁ ካህን የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ ሆይ፥ በርታ፤ እናንተም የአገሩ ሕዝብ ሆይ፥ በርቱ፥ ይላል ጌታ፤ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና ሥሩ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።
2 ጢሞቴዎስ 2:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ልጄ ሆይ! አንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ጸጋ በርታ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ልጄ ሆይ፤ አንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ጸጋ በርታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ልጄ ሆይ! በኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኘው ጸጋ በርታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ልጄ ሆይ! አንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ጸጋ በርታ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ፥ ልጄ ሆይ፥ አንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ጸጋ በርታ። |
አሁን ግን፥ ዘሩባቤል ሆይ፥ በርታ፥ ይላል ጌታ፤ ታላቁ ካህን የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ ሆይ፥ በርታ፤ እናንተም የአገሩ ሕዝብ ሆይ፥ በርቱ፥ ይላል ጌታ፤ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና ሥሩ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።
ልጄ ጢሞቴዎስ ሆይ! አስቀድሞ ስለ አንተ የተነገረውን ትንቢት ሁሉ መሠረት በማድረግ፥ በእነርሱ መልካም ውጊያን እንድትዋጋ ይህችን ትእዛዝ በአደራ ለአንተ እሰጥሃለሁ፤
ነገር ግን ጽና፥ እጅግም በርታ፤ ባርያዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግ ሁሉ ጠብቅ፥ አድርገውም፤ በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ከእርሱ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል።