2 ተሰሎንቄ 2:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ለመዳን እውነቱን ወድደው ባለ መቀበላቸው ለሚጠፉት በማታለል ክፋት ሁሉ ይመጣባቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ይድኑ ዘንድ እውነትን ባለመውደድ የሚጠፉትን ሰዎች በሚያታልል በተለያየ የክፋት ሥራ ይመጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም የሚጠፉትን ሰዎች የሚያታልሉት ማናቸውንም ክፉ ነገሮችን በማድረግ ነው። እነዚህ ሰዎች የሚጠፉትም ለመዳን የሚያበቃቸውን እውነት ወደው ስላልተቀበሉ ነው። |
እንደ እነዚህ ያሉት ሰዎች የገዛ ሆዳቸውን እንጂ ጌታችንን ክርስቶስን አያገለግሉምና፤ በሚያሳምን ንግግርና በሽንገላ የየዋሆችን ልብ ያታልላሉ።
አስቀድማችሁ የኃጢአት ባርያዎች የነበራችሁ፥ ነገር ግን ለተሰጣችሁለት የትምህርት ዓይነት ከልባችሁ በመታዘዛችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።
የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚነግዱ እንደ ብዙዎቹ አይደለንም፤ በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላክን በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን።
ከእንግዲህ እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል፥ በሰዎችም ማታለል ምክንያት፥ በነፈሰው የትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን፥ ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን፥ ሕፃናት መሆን አይገባንም።
ለአሕዛብ እንዳንናገር በመከልከል እነርሱ እንዳይድኑ ያደርጋሉ፤ በዚህም ያለማቋረጥ የኃጢአታቸውን መስፈርያ ይሞላሉ፤ ነገር ግን በመጨረሻ የእግዚአብሔር ቁጣው ይመጣባቸዋል።
በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ! እኛ ግን ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ሁልጊዜ ልናመሰግን ይገባናል፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ከመጀመሪያው አንሥቶ በመንፈስ በመቀደስና በእውነት በማመን እንድትድኑ መርጦአችኋልና፤
ነገር ግን ከእናንተ በኃጢአት ተታሎ ልቡን እምቢተኛ እንዳያደርግ፥ “ዛሬ” ተብሎ የተጠራው ጊዜ እስካለ ድረስ፥ በየቀኑ እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ።
ይሁን እንጂ፥ እነዚህ ግን ለመጠመድና ለመጥፋት እንደ ተወለዱ፥ በፍጥረታዊ ስሜታቸው እንደሚኖሩ አእምሮ እንደሌላቸው እንስሶች ናቸው። የማያውቁትን ነገር እየተሳደቡ፥ ከእነርሱም ጋር አብረው ይጠፋሉ፤