La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 8:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የደማስቆዎቹ ሶርያውያን የጾባን ንጉሥ ሀዳድዔዜርን ለመርዳት በመጡ ጊዜ ዳዊት ሃያ ሁለት ሺህ ሰው ገደለባቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሶርያውያንም የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን ለመርዳት ከደማስቆ በመጡ ጊዜ ዳዊት ሃያ ሁለት ሺሕ ሰው ገደለ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በደማስቆ የሚኖሩ ሶርያውያንም ንጉሥ ሀዳድዔዜርን ለመርዳት ሠራዊት በላኩ ጊዜ ዳዊት አደጋ ጥሎ ኻያ ሁለት ሺህ ጭፍሮችን ገደለ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከደ​ማ​ስ​ቆም ሶር​ያ​ው​ያን የሱ​ባን ንጉሥ አድ​ር​አ​ዛ​ርን ሊረዱ መጡ፤ ዳዊ​ትም ከሶ​ር​ያ​ው​ያን ሃያ ሁለት ሺህ ሰዎ​ችን ገደለ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከደማስቆም ሶርያውያን የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን ሊረዱ በመጡ ጊዜ ዳዊት ከሶርያውን ሀያ ሁለት ሺህ ሰዎች ገደለ።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 8:5
9 Referencias Cruzadas  

አሞናውያን፥ ዳዊት እንደጠላቸው ባወቁ ጊዜ፥ ከቤትረሖብና ከጾባ ሃያ ሺህ ሶርያውያን እግረኛ ወታደሮችን እንዲሁም ንጉሥ መዓካን ከአንድ ሺህ ሰዎቹ ጋር ደግሞም ከጦብ ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎች ቀጠሩ።


ዳዊት በተጨማሪ በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ ያለውን ግዛት መልሶ ለመያዝ በሄደ ጊዜ፥ የጾባን ንጉሥ የረሖብን ልጅ ሀዳድዔዜርን ወጋው።


“እግዚአብሔር ቁጣውን አይመልስም፥ ከእርሱ በታች ረዓብን የሚረዱ ይዋረዳሉ።


ግብጻውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፤ ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም፤ ጌታ እጁን በሚዘረጋ ጊዜ፥ ረጂው ይሰናከላል ተረጂውም ይወድቃል፥ ሁሉም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።


የሶርያ ራስ ደማስቆ፤ የደማስቆ ራስ ረአሶን ነውና፤ በሥልሳ አምስት ዓመት ውስጥ፤ የኤፍሬም ሕዝብ ይበታተናል፤ ሕዝብ መሆኑም ይቀራል።