La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 21:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነገር ግን ንጉሡ የአያ ልጅ ሪጽፋ ለሳኦል የወለደቻቸውን ሁለቱን ወንዶች ልጆች አርሞኒንና መፊቦሼትን፤ የሳኦል ልጅ ሜራብ ለመሖላታዊው ለባርዚላይ ልጅ ለአድሪኤል የወለደችለትን አምስት ወንዶች ልጆች ጭምር ወሰደ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ነገር ግን ንጉሡ፣ የኢዮሄል ልጅ ሪጽፋ ለሳኦል የወለደቻቸውን ሁለቱን ወንዶች ልጆች ሄርሞንንና ሜምፊቦስቴን፤ የሳኦል ልጅ ሜሮብ ለመሓላታዊው ለቤርዜሊ ልጅ ለኤስድሪኤል የወለደችለትን ዐምስት ወንዶች ልጆች ጭምር ወሰደ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይሁን እንጂ ዳዊት የአያ ልጅ ሪጽፋ ለሳኦል የወለደቻቸውን ሁለቱን ወንዶች ልጆች አርሞኒንና መፊቦሼትን ወሰደ፤ እንዲሁም የሳኦል ልጅ ሜራብ የመሖላን ተወላጅ ለሆነው ለባርዚላይ ልጅ ለዐድሪኤል የወለደችለትን አምስት ወንዶች ልጆች ጨምሮ ወሰደ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ንጉ​ሡም ለሳ​ኦል የወ​ለ​ደ​ቻ​ቸ​ውን የኢ​ዮ​ሄ​ልን ልጅ የሩ​ጻ​ፋን ሁለ​ቱን ልጆች ሄር​ሞ​ን​ስ​ቴ​ንና ሜም​ፌ​ቡ​ስ​ቴን፥ ለመ​ሓ​ላ​ታ​ዊ​ውም ለቤ​ር​ዜሊ ልጅ ለኤ​ስ​ድራ የወ​ለ​ደ​ቻ​ቸ​ውን የሳ​ኦ​ልን ልጅ የሜ​ሮ​ብን አም​ስ​ቱን ልጆች ወሰደ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ንጉሡም ለሳኦል የወለደቻቸውን የኢዮሄል ልጅ የሪጽፋን ሁለቱን ልጆች ሄርሞንንና ሜምፊቦስቴን ለመሓላታዊውም ለቤርዜሊ ልጅ ለኤስድሪኤል የወለደቻቸውን የሳኦልን ልጅ የሜሮብን አምስቱን ልጆች ወሰደ፥

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 21:8
4 Referencias Cruzadas  

ሳኦልም ሪጽፋን የምትባለውን የአያን ልጅ በዕቁባትነት አስቀምጦአት ነበር፤ ኢያቡስቴም አበኔርን፥ “ለምንድን ነው ከአባቴ ዕቁባት ጋር የተኛኸው?” አለው።


የኒምሺን ልጅ ኢዩንም ቀብተህ በእስራኤል ላይ አንግሠው፤ የአቤል መሖላ ተወላጅ የሆነውን የዮሣፋጥን ልጅ ኤልሳዕንም ቀብተህ በአንተ እግር ነቢይ እንዲሆን አድርገው።


የሳኦል ወንዶች ልጆች ዮናታን፥ ይሽዊና ማልኪሹዓ ነበሩ፤ ሴቶች ልጆቹም ትልቋ ሜሮብ፥ ትንሿ ሜልኮል ይባሉ ነበር።


ይሁን እንጂ የሳኦል ልጅ ሜራብ ለዳዊት የምትዳርበት ጊዜ ሲደርስ ለመሓላታዊው ለኤድሪኤል ተዳረች።