2 ጴጥሮስ 1:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ወንድሞች ሆይ! መጠራታችሁንና መመረጣችሁን እንድታጸኑ፥ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ ይህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፤ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ለማጽናት ከፊት ይልቅ ትጉ፤ ምክንያቱም እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ወንድሞች ሆይ! መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ለማረጋገጥ በይበልጥ የምትጓጉ ሁኑ፤ ይህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ወንድሞች ሆይ! መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና። |
ሆኖም የእግዚአብሔር ጠንካራ መሠረት የቆመው፦ “ጌታ የራሱ የሆኑትን ያውቃል፤” እንዲሁም “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዐመፅ ይራቅ፤” የሚለውን ማኅተም ታትሞ ነው።
ወደ ኢያሱም ተመልሰው እንዲህ አሉት፦ “ሁለት ወይም ሦስት ሺህ ያህል ሰው ወጥተው ጋይን ይምቱ እንጂ ሕዝቡ ሁሉ አይውጣ፤ ጥቂቶች ናቸውና ሕዝቡ ሁሉ ወደዚያ ለመሄድ አይድከም።”
እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ ያወቃችሁ፥ በመንፈስ የተቀደሳቹ፥ ለኢየሱስ ክርስቶስ ትታዘዙና በደሙም ትረጩ ዘንድ ለተመረጣችሁት፥ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።