2 ነገሥት 4:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከነቢያቱም አንዱ ጎመን የሚመስል ቅጠላ ቅጠል ለመልቀም ወደ ሜዳ ሔደ፤ እርሱም በዱር ውስጥ የበቀለ የቅል ሐረግ አገኘ፤ መሸከም የሚችለውን ያኽል በርከት ያለ ቅል ቆርጦ አመጣ፤ የዚያንም ምንነት ሳያውቅ ከትፎ ወጡ ውስጥ ጨመረው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእነርሱም አንዱ ቅጠላ ቅጠል ለማምጣት ወደ ሜዳ ወጥቶ፤ ዱር በቀል ሐረግ አገኘ፤ ከሐረጉም ላይ የቅል ፍሬ ለቅሞ በልብሱ ሙሉ ይዞ ተመለሰና ቈራርጦ በወጡ ምንቸት ውስጥ ጨመረው፤ ምን እንደ ሆነ ግን ማንም አላወቀም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከነቢያቱም አንዱ ጎመን የሚመስል ቅጠላ ቅጠል ለመልቀም ወደ ሜዳ ሔደ፤ እርሱም በዱር ውስጥ የበቀለ የቅል ሐረግ አገኘ፤ መሸከም የሚችለውን ያኽል በርከት ያለ ቅል ቈርጦ አመጣ፤ የዚያንም ምንነት ሳያውቅ ከትፎ ወጡ ውስጥ ጨመረው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንዱም ቅጠላ ቅጠል ያመጣ ዘንድ ወደ ሜዳ ወጣ፤ በምድረ በዳውም የወይን ቦታ አገኘ፤ ከዚያም የምድር ቅጠላ ቅጠል ሰብሰበ፤ ልብሱንም ሞላ፤ መትሮም በወጡ ምንቸት ውስጥ ጨመረው፤ አበሰለውም፤ ምን እንደ ሆነ ግን አላወቁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንዱም ቅጠላቅጠል ያመጣ ዘንድ ወደ ሜዳ ወጣ፤ የምድረ በዳውንም ሐረግ አገኘ፤ ከዚያም የበረሃ ቅል ሰበሰበ፤ ልብሱንም ሞልቶ ተመለሰ፤ መትሮም በወጡ ምንቸት ውስጥ ጨመረው፤ ምን እንደ ሆነ ግን አላወቁም። |
የሊባኖስ ዛፍ እንጨት ሳንቃዎች በአበባ እንቡጦችና በፈኩ አበባዎች ቅርጽ አጊጠው ነበር፤ ውስጡም ሁሉ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ ስለ ተለበደ የግንቡ ድንጋዮች አይታዩም ነበር።
በመላ አገሪቱ ራብ በነበረበት በአንድ ወቅት ኤልሳዕ ወደ ጌልጌላ ተመልሶ መጣ፤ በዚያም የነቢያትን ጉባኤ በማስተማር ላይ ሳለ አገልጋዩን “ትልቅ ድስት ጥደህ ወጥ ሥራላቸው” አለው።
እኔ የተመረጠች ወይን ፍጹምም እውነተኛ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር፤ አንቺ ግን የተበላሸ የእንግዳ ወይን ግንድ ሆነሽ እንዴት ተለወጥሽብኝ?