ፈርዖንም ዮሴፍን “ጸፍናት ፐዕናህ” ብሎ ስም አወጣለት። እንዲሁም የሄልዮቱጠ ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናትን አጋባው። ዮሴፍም በመላዪቱ የግብጽ ምድር ተዘዋወረ።
2 ነገሥት 23:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሥ ኒካዑ የኢዮስያስ ልጅ ኤልያቄም በአባቱ በኢዮስያስ እግር ተተክቶ በይሁዳ እንዲነግሥ አደረገ፤ ስሙንም በመለወጥ ኢዮአቄም ብሎ ጠራው፤ ኢዮአሐዝም በንጉሥ ነኮ ተማርኮ ወደ ግብጽ ተወሰደ፤ በዚያም ሞተ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈርዖን ኒካዑ የኢዮስያስን ልጅ ኤልያቄምን በአባቱ በኢዮስያስ እግር አነገሠው፤ ኤልያቄም የተባለ ስሙንም ለውጦ ኢዮአቄም አለው። ነገር ግን ኢዮአካዝን በምርኮ ወደ ግብጽ ወሰደው፤ እርሱም በዚያ ሞተ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ኒካዑ የኢዮስያስ ልጅ ኤልያቄም በአባቱ በኢዮስያስ እግር ተተክቶ በይሁዳ እንዲነግሥ አደረገ፤ ስሙንም በመለወጥ ኢዮአቄም ብሎ ጠራው፤ ኢዮአሐዝም በንጉሥ ነኮ ተማርኮ ወደ ግብጽ ተወሰደ፤ በዚያም ሞተ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖን ኒካዑም የይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስን ልጅ ኤልያቄምን በአባቱ በኢዮስያስ ፋንታ አነገሠ፤ ስሙንም ኢዮአቄም ብሎ ለወጠው። ዮአክስንም ወስዶ ወደ ግብፅ አፈለሰው፤ በዚያም ሞተ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖን ኒካዑም የኢዮስያስን ልጅ ኤልያቄምን በአባቱ በኢዮስያስ ፋንታ አነገሠ፤ ስሙንም ኢዮአቄም ብሎ ለወጠው። ኢዮአካዝንም ወስዶ ወደ ግብጽ አፈለሰው፤ በዚያም ሞተ። |
ፈርዖንም ዮሴፍን “ጸፍናት ፐዕናህ” ብሎ ስም አወጣለት። እንዲሁም የሄልዮቱጠ ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናትን አጋባው። ዮሴፍም በመላዪቱ የግብጽ ምድር ተዘዋወረ።
በኢዮስያስ ዘመነ መንግሥት ነኮ የተባለው የግብጽ ንጉሥ የአሦርን ንጉሠ ነገሥት ለመርዳት ሠራዊቱን እየመራ ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ተጓዘ፤ ንጉሥ ኢዮስያስም መጊዶ ላይ የግብጽን ሠራዊት ለማገድ ጦርነት ገጥሞ በዚያ ውጊያ ላይ ተገደለ፤
በይሁዳም ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን፥ እስከ ይሁዳ ንጉሥ እስከ ኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያስ ዐሥራ አንደኛው ዓመት ፍጻሜ፥ ኢየሩሳሌም እስከ ተማረከችበት እስከ አምስተኛው ወር ድረስ መጣ።