2 ነገሥት 18:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታዲያ ይህ ከሆነ የሐማትና የአርፋድ አማልክት የት አሉ? የሰፋርዋይም የሄናዕና የዒዋ አማልክትስ የት ደረሱ? ከእነርሱ አንዱ እንኳ ሰማርያን ከእጄ ማዳን ችሎአልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሐማትና የአርፋድ አማልክት ወዴት አሉ? የሴፈርዋይም፣ የሄናና የዒዋም አማልክት ታዲያ የት ደረሱ? ሰማርያን ከእጄ አድነዋታልን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ ይህ ከሆነ የሐማትና የአርፋድ አማልክት የት አሉ? የሰፋርዋይም የሄናዕና የዒዋ አማልክትስ የት ደረሱ? ከእነርሱ አንዱ እንኳ ሰማርያን ከእጄ ማዳን ችሎአልን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኤማትና የአርፋድ አማልክት ወዴት አሉ? የሴፋሩዋይምና የሄና የዒዋም አማልክት ወዴት አሉ? ስማርያን ከእጄ አድነዋታልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሐማትና የአርፋድ አማልክት ወዴት አሉ? የሴፈርዋይምና የሄና የዒዋም አማልክት ወዴት አሉ? ሰማርያን ከእጄ አድነዋታልን? |
ይኸውም ሆሴዕ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት ሰልምናሶር ድል አድርጎ ሰማርያን ያዘ፤ እስራኤላውያንንም ማርኮ በእስረኛነት ወደ አሦር ወሰዳቸው፤ ከእነርሱም ጥቂቶቹ በሐላሕ ከተማ፥ ጥቂቶቹ በጎዛን አውራጃ ውስጥ በሚገኘው በሐቦር ወንዝ አጠገብ፥ እንዲሁም ሌሎቹ በሜዶን ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ።
ወደ ካልኔ እለፉና ተመልከቱ፤ ከዚያም ወደ ታላቂቱ ሐማት ሂዱ፤ ከዚያም ወደ ፍልስጥኤም ጌት ውረዱ፤ እነርሱ ከእነዚህ መንግሥታት ይሻላሉን? ወይስ ድንበራቸው ከድንበራችሁ ይሰፋልን?