Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ነገሥት 18:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 የእነዚህ ሁሉ አገሮች አማልክት ከንጉሠ ነገሥታቶቻችን እጅ አገሮቻቸውን ለማዳን የቻሉበት ጊዜ አለን? ታዲያ እንግዲህ እናንተ ‘እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ያድናታል’ ብላችሁ የምታስቡት እንዴት ነው?”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ከእነዚህ አገሮች አማልክት ሁሉ አገሩን ከእጄ የታደገ ማን አለ? ታዲያ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን እንዴት ከእጄ ሊታደጋት ይችላል?”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 የእነዚህ ሁሉ አገሮች አማልክት ከንጉሠ ነገሥታቶቻችን እጅ አገሮቻቸውን ለማዳን የቻሉበት ጊዜ አለን? ታዲያ እንግዲህ እናንተ ‘እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ያድናታል’ ብላችሁ የምታስቡት እንዴት ነው?”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ከእጄ ያድ​ናት ዘንድ ከሀ​ገ​ሮቹ አማ​ል​ክት ሁሉ ሀገ​ሩን ከእጄ ያዳነ ማን ነው?”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ከእጄ ያድን ዘንድ ከአገሮቹ አማልክት ሁሉ አገሩን ከእጄ ያዳነ ማን ነው?’”

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 18:35
13 Referencias Cruzadas  

መጥረቢያ በሚቆርጥበት ሰው ላይ ይኩራራልን? መጋዝስ በሚስበው ላይ ይታበያልን? በትር በሚያነሣው ሰው ላይ ራሱን እንደሚነቀንቅ፤ ዘንግም ዕንጨት እንዳልሆነ አድርጎ እንደሚኩራራ ነው።


አሁንም ሕዝቅያስ አያስታችሁ፥ እንዲህም አያባብላችሁ፥ አትመኑትም፤ ከአሕዛብና ከመንግሥታት አማልክት ሁሉ ሕዝቡን ከእጄና ከአባቶቼ እጅ ለማዳን ማንም አልቻለም፤ ይልቁንስ አምላካችሁ ከእጄ ሊያድናቸሁ እንዴት ይችላል?’ ”


እግዚአብሔር ሆይ፥ የአሦር ነገሥታት ብዙ ሕዝቦችና ምድራቸውን መደምሰሳቸው እርግጥ ነው።


ፈርዖንም፦ “ቃሉን እንድሰማ እስራኤልንስ እንድለቅ ጌታ ማን ነው? ጌታን አላውቅም፥ እስራኤልንም ደግሞ አልለቅቅም” አለ።


ሕዝቡም ቀደም ሲል ንጉሥ ሕዝቅያስ ባዘዛቸው መሠረት አንዲት ቃል ሳይናገሩ ዝም አሉ፤


የአሦር ንጉሠ ነገሥት ሕያው እግዚአብሔርን እንዲሰድብለት ከፍተኛ ባለሥልጣኑን ልኮአል፤ አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ስድብ ሰምቶ ተሳዳቢውን ይቀጣ ይሆናል፤ ስለዚህ ከሕዝባችን መካከል በሕይወት ለተረፉት ሰዎች እባክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ።”


ማታ ይመለሱ እንደ ውሾችም ያላዝኑ፥ በከተማም ይዙሩ።


እኔ ግን ጌታ፥ ከግብጽ ምድር ጀምሬ አምላክህ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ አታውቅም፥ ከእኔም በቀር ሌላ አዳኝ የለም።


የአሦር ነገሥታት አገሮችን ሁሉ እንዴት ፈጽመው እንደ ደመሰሱ ሰምተሃል፤ አንተስ የምታመልጥ ይመስልሃልን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios