2 ነገሥት 12:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሆኖም ከብር ለሚሠሩ ጐድጓዳ ሳሕኖች፥ የዐመድ ማጠራቀሚያ፥ ጐድጓዳ ወጭት፥ እምቢልታ ወይም ደግሞ ከብርም ሆነ ከወርቅ ለሚሠሩ ንዋያተ ቅድሳት ከዚያ ገንዘብ ላይ ተነሥቶ የሚከፈል ሒሳብ አልነበረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለቤተ መቅደሱ ከገባው ገንዘብ ግን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ግልጋሎት ለሚውሉ የብር ጽዋዎች፣ መኰስተሪያዎች፣ ድስቶች፣ መለከቶችና ወይም ለሌሎች የወርቅም ሆነ የብር ዕቃዎች መሥሪያ አልዋለም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሆኖም ከብር ለሚሠሩ ጐድጓዳ ሳሕኖች፥ የዐመድ ማጠራቀሚያ፥ ጐድጓዳ ወጭት፥ እምቢልታ ወይም ደግሞ ከብርም ሆነ ከወርቅ ለሚሠሩ ንዋያተ ቅድሳት ከዚያ ገንዘብ ላይ ተነሥቶ የሚከፈል ሒሳብ አልነበረም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር ቤት ከሚመጣው ገንዘብ ለእግዚአብሔር ቤት የሚሆኑ የብር መዝጊያዎች፥ ጽዋዎችና ጕጠቶች፥ ድስቶችም፥ መለከቶችም፥ የወርቅና የብር ዕቃዎችም አልተሠሩም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተናደውን የእግዚአብሔርን ቤት ለመጠገን መክፈል ለሚያሻው ሁሉ ድንጋይና እንጨት ይገዙ ዘንድ የእግዚአብሔርን ቤት ለሚሠሩ አናጢዎችና ሠራተኞች፥ ግንበኞችና ድንጋይ ወቃሪዎች ይሰጡት ነበር። |
በጨረሱም ጊዜ የተረፈውን ገንዘብ በንጉሡና በዮዳሄ ፊት አመጡ፤ በእርሱም ለጌታ የቤት ዕቃ፥ የአገልግሎትና የቁርባን ዕቃ፥ ሙዳዮቹም፥ የወርቅና የብርም ዕቃ ተሠራበት። በዮዳሄም ዘመን ሁሉ በጌታ ቤት የሚቃጠል መሥዋዕት ሁልጊዜ ያቀርቡ ነበር።
ለጠራቢዎችና ለአናጢዎችም ገንዘብ ሰጡ፤ የፋርስም ንጉሥ ቂሮስ እንደ ፈቀደላቸው የዝግባ ዛፍ ከሊባኖስ ወደ ያፎ ባሕር እንዲያመጡ ለሲዶናውያንና ለጢሮሳውያን መብልና መጠጥ ዘይትም ሰጡ።
“ሁለት የብር መለከቶች ሥራ፤ እነርሱንም ተቀጥቅጦ በሚሠራ ሥራ ለራስህ አብጃቸው፤ ማኅበሩን ለመጥራት ከሰፈራቸውም ተነሥተው እንዲጓዙ ለመቀስቀስ ተጠቀምባቸው።