ይህም፥ “በተነ፤ ለድኾችም ሰጠ፤ ጽድቁ ለዘለዓለም ይኖራል፤” ተብሎ ተጽፏል።
ይህም፣ “በተነ፤ ለድኾችም ሰጠ፤ ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።
ይህም፦ “ለድኾች በልግሥና ሰጠ፤ ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።
“በተነ፤ ለድሃም ሰጠ፤ ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል” ብሎ መጽሐፍ እንደ ተናገረ።
ክብርና ሀብት በቤቱ ነው፥ ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል።
በተነ፥ ለችግረኞችም ሰጠ፥ ጽድቁ ለዘለዓለም ዓለም ይኖራል፥ ቀንዱም በክብር ከፍ ከፍ ይላል።
ጽድቅንና ምሕረትን የሚከተል ሕይወትንና ጽድቅን ክብርንም ያገኛል።
ብልጥግናና ክብር በእኔ ዘንድ ነው፥ ብዙ ሀብትና ጽድቅም።
እንደ ልብስም ብል ይበላቸዋል፥ እንደ በግ ጠጉርም ትል ይበላቸዋል፤ ጽድቄ ግን ለዘለዓለም ማዳኔም ለትውልድ ሁሉ ይሆናል።
እንግዲህ እምነት፥ ተስፋ፥ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው።
ለዘሪ ዘርን፥ ለመብላትም እንጀራን የሚሰጥ፥ እርሱ የምትዘሩትን ዘር ይሰጣችኋል፤ ያበረክትላችሁማል፤ የጽድቃችሁንም ፍሬ ያሳድጋል፤