ከሳዶቅም ወገን የሆነ ታላቁ ካህን ዓዛርያስ፦ “ሕዝቡ ቁርባኑን ወደ ጌታ ቤት ማቅረብ ከጀመረ ወዲህ በልተናል፥ ጠግበናልም፥ ጌታ ሕዝቡን ባርኮአልና ብዙ ተርፎአል፤ የተረፈውም ይህ ክምር ትልቅ ነው” ብሎ ተናገረ።
2 ቆሮንቶስ 9:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእኛ በኩል እግዚአብሔርን የማመስገኛ ምክንያት የሚሆነውን ልግስናችሁ በሁሉ ነገር ባለ ጠጎች ያደርጋችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁልጊዜ በልግስና መስጠት እንድትችሉ በሁሉ ነገር ያበለጽጋችኋል፤ ልግስናችሁም በእኛ በኩል የሚደርሳቸው ሰዎች እግዚአብሔርን ለማመስገን ምክንያት ይሆናቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልግሥናችሁ በእኛ አማካይነት የሚደርሳቸው ሰዎች ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ዘንድ ሁልጊዜ እንድትለግሡ እግዚአብሔር በሁሉ ነገር ያበለጽጋችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለብዙ ሰዎች ስለ ሰጣችሁም የእግዚአብሔርን ምስጋና በምታደርግላችሁ ልግስና ሁሉ ባለጸጎች ትሆናላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእኛ በኩል ለእግዚአብሔር የምስጋና ምክንያት የሚሆነውን ልግስና ሁሉ እንድታሳዩ በሁሉ ነገር ባለ ጠጎች ትሆናላችሁ። |
ከሳዶቅም ወገን የሆነ ታላቁ ካህን ዓዛርያስ፦ “ሕዝቡ ቁርባኑን ወደ ጌታ ቤት ማቅረብ ከጀመረ ወዲህ በልተናል፥ ጠግበናልም፥ ጌታ ሕዝቡን ባርኮአልና ብዙ ተርፎአል፤ የተረፈውም ይህ ክምር ትልቅ ነው” ብሎ ተናገረ።
ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን የጌታን የራሱን ክብርና የእኛን በጎ ፈቃድ ለማሳየት በምናገለግለው በዚህ የቸርነት ሥራ ከእኛ ጋር አብሮን እንዲሄድ በአብያተ ክርስቲያናት ተመርጧል።