“በአራት ጋን ውሃ ሞልታችሁ በመሥዋዕቱና በእንጨቱ ላይ አፍስሱት!” አላቸው፤ እነርሱም እንዲሁ አደረጉ፤ “አሁንም ጨምሩበት!” አላቸው፤ እነርሱም እንዲሁ አደረጉ፤ እርሱም “አሁንም እንደገና አንድ ጊዜ ጨምሩ!” አላቸው፤ እነርሱም እንዲሁ አደረጉ።
2 ቆሮንቶስ 8:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክንያቱም በጌታ ፊት ብቻ ያልሆነ፥ ነገር ግን በሰው ፊት ደግሞ መልካም የሆነውን ስለምናስብ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም ዐላማችን በጌታ ፊት ብቻ ሳይሆን፣ በሰውም ፊት መልካም የሆነውን ነገር ማድረግ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዓላማችን በጌታ ፊት ብቻ ሳይሆን በሰዎችም ፊት መልካም የሆነውን ነገር ማድረግ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ፊት ብቻ ያይደለ፥ ነገር ግን በሰው ፊትም መልካሙን ነገር እናስባለንና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጌታ ፊት ብቻ ያይደለ ነገር ግን በሰው ፊት ደግሞ መልካም የሆነውን እናስባለንና። |
“በአራት ጋን ውሃ ሞልታችሁ በመሥዋዕቱና በእንጨቱ ላይ አፍስሱት!” አላቸው፤ እነርሱም እንዲሁ አደረጉ፤ “አሁንም ጨምሩበት!” አላቸው፤ እነርሱም እንዲሁ አደረጉ፤ እርሱም “አሁንም እንደገና አንድ ጊዜ ጨምሩ!” አላቸው፤ እነርሱም እንዲሁ አደረጉ።
“ሰዎች እንዲያዩላችሁ ብላችሁ መልካምም ሥራችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ አለበለዚያ በሰማያት ካለው አባታችሁ ዘንድ ሽልማት አታገኙም።
የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚነግዱ እንደ ብዙዎቹ አይደለንም፤ በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላክን በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን።
በብዙ ነገር ተፈትኖና በብዙ ጉዳዮች ትጉህ ሆኖ ያገኘነውን ወንድማችንን ከእነርሱ ጋር ልከነዋል። አሁንም በእናንተ እጅግ ስለሚታመን ከበፊት ይልቅ እጅግ ትጉህ ነው።
በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ክቡር የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ምስጉን የሆነውን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤
እንግዲህ ወጣት መበለታት እንዲያገቡ፥ ልጆችንም እንዲወልዱ፥ እያንዳንዳቸውም ቤተሰቦቻቸውን እንዲያስተዳድሩ እፈቅዳለሁ፤ በዚህም ተቃዋሚ የሚሳደብበትን ምንም ዓይነት ሰበብ እንዳይሰጡት ነው፤
ምናልባት “ክፉ አድራጊዎች ናቸው” ብለው ቢያሙአችሁም እንኳ እግዚአብሔር በሚጎበኝበት ቀን፥ ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ እርሱን እንድያከብሩት በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።
እስኪነጋም በእግርጌው ተኛች፥ ቦዔዝም፦ “ሴት ወደ አውድማው እንደ መጣች ማንም እንዳያውቅ” ብሎ ነበርና ማንም ሊያያት በማይችልበት ሰዓት በማለዳ ከመኝታዋ ተነሣች።