2 ቆሮንቶስ 7:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመምጣቱም ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን ናፍቆታችሁንና ልቅሶአችሁን ስለ እኔም የነበራችሁን ቅንዓት ሲነገረን በእናንተ ስለተጽናናን ማለቴ ነው፤ ስለዚህም ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ደስ አለኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተጽናናነውም በመምጣቱ ብቻ ሳይሆን፣ እርሱንም ልታጽናኑት በመቻላችሁ ጭምር ነው። ስለ ናፍቆታችሁ፣ ስለ ሐዘናችሁና ለእኔም ስላላችሁ ቅናት ነግሮናል፤ ስለዚህ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ደስ ብሎኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተጽናናነውም በእርሱ መምጣት ብቻ ሳይሆን እናንተ እርሱን ያጽናናችሁት መሆኑን በመስማታችንም ጭምር ነው፤ ስለ እኔ ያላችሁን ናፍቆትና ሐዘን ጭንቀትም በነገረን ጊዜ ይበልጥ ደስ አለኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመምጣቱ ብቻ አይደለም፤ በአጽናናችሁት ማጽናናትም ነው እንጂ፤ ለእኛ እንደምታስቡና እንደምትቀኑ ፍቅራችሁን ነግሮናል፤ ይህንም ሰምቼ ደስታዬ በእናንተ በዛ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመምጣቱም ብቻ አይደለም ነገር ግን ናፍቆታችሁንና ልቅሶአችሁን ስለ እኔም ቅንዓታችሁን ሲናገረን በእናንተ ላይ በተጽናናበት መጽናናት ደግሞ ነው፤ ስለዚህም ከፊት ይልቅ ደስ አለን። |
ይህ ናፍቆቴ ተስፋዬም ነውና፤ በምንም ዓይነት ነገር አላፍርም፤ ነገር ግን በሕይወት ብኖር ወይም ብሞት፥ ክርስቶስ እንደ ወትሮው እንዲሁ አሁንም በሥጋዬ ይከብራል ብዬ በሙሉ ድፍረት እናገራለሁ።
በአካል ምንም እንኳ ብርቅ፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝና፤ መልካሙንም ሥነ ሥርዓታችሁንና በክርስቶስም ላይ ያላችሁን የእምነታችሁን ጽናት እያየሁ ደስ ይለኛል።
አሁን ግን ጢሞቴዎስ ከእናንተ ዘንድ ወደ እኛ መጥቶ ስለ እምነታችሁና ስለ ፍቅራችሁ መልካም ዜና አመጣልን፤ እኛ እናንተን ለማየት እንደምንናፍቅ እናንተም እኛን ለማየት እንደምትናፍቁና ሁልጊዜ በመልካም እንደምታስታውሱን ደግሞ ነገረን፤
ወዳጆች ሆይ! ስለ ጋራ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለቅዱሳን ሁሉ ስለ ተሰጠው እምነት እንድትጋደሉ እንድመክራችሁና እንድጽፍላችሁ ግድ ሆነብኝ።