2 ቆሮንቶስ 3:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ የሙሴ መጻሕፍት በተነበቡ ቍጥር ያ መጋረጃ በልባቸው ይኖራል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስከ ዛሬም ድረስ የሙሴ መጻሕፍት በተነበቡ ቍጥር መሸፈኛው ልቡናቸውን ይሸፍናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዛሬም እንኳ ቢሆን የሕግ መጻሕፍትን ባነበቡ ቊጥር ልቡናቸው በመሸፈኛው ይሸፈናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስከ ዛሬም የሙሴን ሕግ ሲያነብቡ ያ መጋረጃ ልባቸውን ይሸፍናቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ የሙሴ መጻሕፍት በተነበቡ ጊዜ ሁሉ ያ መጋረጃ በልባቸው ይኖራል፤ |