2 ቆሮንቶስ 3:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይሻር የነበረውን መጨረሻ ትኩር ብለው የእስራኤል ልጆች እንዳይመለከቱ፥ ፊቱን እንደ ጋረደው እንደ ሙሴ አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን የፊቱ ማንጸባረቅ እየጠፋ ሲሄድ መጨረሻውን እንዳይመለከቱ፣ ፊቱን በጨርቅ እንደ ሸፈነው እንደ ሙሴ አይደለንም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ እየከሰመ የሚሄደው የፊቱ መንጸባረቅ እስኪወገድ ድረስ እስራኤላውያን እንዳያዩ ፊቱን ይሸፍን ነበር፤ እኛ ግን እንደ እርሱ አይደለንም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዚያን ይሻር የነበረውን መጨረሻ፥ የእስራኤል ልጆች እንዳያዩት ፊቱን ይሸፍን እንደ ነበረው እንደ ሙሴ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዚያንም ይሻር የነበረውን መጨረሻ ትኵር ብለው የእስራኤል ልጆች እንዳይመለከቱ፥ በፊቱ መጋረጃ እንዳደረገ እንደ ሙሴ አይደለንም። |
ዳሩ ግን የእስራኤል ልጆች ስለዚያ ስለ ተሻረው፥ ስለ ፊተኛው ክብር የሙሴን ፊት ትኩር ብለው መመልከት እስኪሳናቸው ድረስ፥ ያ በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸ የሞት አገልግሎት ያን ያህል ክቡር ከሆነ፥