እኔ ነፍሴን በፈቃዴ አሳልፌ እሰጣለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። አሳልፌ ለመስጠት ሥልጣን አለኝ፤ መልሼ ለመውሰድም ሥልጣን አለኝ፤ ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ።”
2 ቆሮንቶስ 13:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በድካም ተሰቅሎአል፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ኃይል በሕይወት ይኖራል። እኛ ደግሞ ከእርሱ ጋር ደካሞች ብንሆን፤ እናንተ ለማገልገል በእግዚአብሔር ኃይል ከእርሱ ጋር በሕይወት እንኖራለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተሰቀለው በድካም ቢሆንም፣ በእግዚአብሔር ኀይል ሕያው ሆኖ ይኖራል። እኛም በርሱ ደካሞች ብንሆንም፣ እናንተን ለማገልገል ግን በእግዚአብሔር ኀይል ከርሱ ጋራ ሕያዋን ሆነን እንኖራለን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የሞተው በደካማነት ቢሆንም አሁን በእግዚአብሔር ኀይል በሕይወት ይኖራል፤ እኛም ከእርሱ ጋር ደካሞች ሆነናል፤ ከእናንተ ጋር ባለን ግንኙነት ግን ከእርሱ ጋር በእግዚአብሔር ኀይል እንኖራለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በድካም ተሰቅሎአልና፤ በእግዚአብሔርም ኀይል ሕያው ነውና፤ እኛም ከእርሱ ጋር እንደክማለንና፤ ነገር ግን ስለ እናንተ በሚሆን በእግዚአብሔር ኀይል ከእርሱ ጋር በሕይወት እንኖራለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በድካም ተሰቅሎአልና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ኃይል በሕይወት ይኖራል። እኛ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንደክማለንና፥ ነገር ግን ስለ እናንተ በሆነ በእግዚአብሔር ኃይል ከእርሱ ጋር በሕይወት እንኖራለን። |
እኔ ነፍሴን በፈቃዴ አሳልፌ እሰጣለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። አሳልፌ ለመስጠት ሥልጣን አለኝ፤ መልሼ ለመውሰድም ሥልጣን አለኝ፤ ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ።”
በስሙም በማመን ይህን የምታዩትንና የምታውቁትን የእርሱ ስም አጸናው፤ በእርሱም በኩል የሆነው እምነት በሁላችሁ ፊት ይህን ፍጹም ጤና ሰጠው።
ስለዚህ በአብ ክብር ክርስቶስ ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንኖር፥ በጥምቀት አማካኝነት በሞት ከእርሱ ጋር ተቀብረናል።
እርሱም ሥጋ ለብሶ በምድር በሚመላለስ ጊዜ፥ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል፥ ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፤ ስለ ጻድቅ ፍርሃቱም ጸሎቱ ተሰማለት፤
ክርስቶስ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዐመፀኞች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስለ ኃጢአት መከራን ተቀበለ፤ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርባችሁ በሥጋ ሞተ፥ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ።