እምነታችሁ ምክንያት አድርገን እናንተን ገዢዎች አይደለንም፤ ይልቁን በእምነታችሁ ጸንታችሁ ቆማችኋልና ለደስታችሁ ከእናንተ ጋር የምንሠራ ነን።
2 ቆሮንቶስ 10:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሥልጣናችን ከበፊቱ ይልቅ አሁን ብመካም እንኳን፥ ይህን ጌታ የሰጠን እናንተን ለማነጽ እንጂ እናንተን ለማፍረስ ስላልሆነ አላፍርበትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ በሰጠን ሥልጣን እጅግ ብመካም በዚህ አላፍርም፤ ሥልጣኑን የተቀበልነው እናንተን ለማነጽ እንጂ ለማፍረስ አይደለምና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታ ስለ ሰጠን ሥልጣን በጣም ብመካም አላፍርበትም፤ ይህ ሥልጣን የተሰጠን እናንተን ለማነጽ እንጂ ለማፍረስ አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተን ለማነጽ እንጂ፥ እናንተን ለማፍረስ ያይደለ፥ እግዚአብሔር በእናንተ ላይ በሰጠን ሥልጣን እጅግ የተመካሁት መመካት ቢኖር አላፍርም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ እናንተን ለማነጽ እንጂ እናንተን ለማፍረስ ያይደለ በሰጠው በሥልጣናችን ከፊት ይልቅ ብመካ እንኳ አላፍርም። |
እምነታችሁ ምክንያት አድርገን እናንተን ገዢዎች አይደለንም፤ ይልቁን በእምነታችሁ ጸንታችሁ ቆማችኋልና ለደስታችሁ ከእናንተ ጋር የምንሠራ ነን።
ለእናንተ ስለ ራሳችን ሁልጊዜ መልስ የምንሰጥ ይመስላችኋልን? በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን፤ ነገር ግን፥ ወዳጆቼ! እናንተን ለማነጽ ስንል ሁሉን እንናገራለን።
ልመካ ብፈልግ አልሞኝም፤ ምክንያቱም የምናገረው እውነት ነው፤ ነገር ግን ማንም ስለ እኔ ከሚያየውና ከሚሰማው ባለፈ የበለጥኩ አድርጎ እንዳያስበኝ ይህን ከመናገር እቆጠባለሁ።
ከእናንተ ርቄ ሳለሁ እነዚህን ነገሮች የምጽፍላችሁ ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ ሥልጣኔን በኃይል እንዳልጠቀም ነው፤ ጌታም ይህን ሥልጣን የሰጠኝ እናንተን ለማነጽ እንጂ ለማፍረስ አይደለም።
በእርሱ ፊት ስለ እናንተ በተመካሁበት ነገር አላሳፈራችሁኝም፤ ነገር ግን ሁሉን ለእናንተ የተናገርነው እውነት እንደሆነ ሁሉ፥ እንደዚሁም ትምክህታችን በቲቶ ፊት እውነት ሆነ።
ስለ እናንተ እምነቴ ታላቅ ነው፤ በእናንተ ምክንያት ትምክህቴ ታላቅ ነው፤ እኔም በመጽናናት ተሞልቻለሁ፤ በመከራችን ሁሉ ደስታዬ ወሰን የለውም።
በዚህም ምክንያት ይህን መከራ ደግሞ እቀበላለሁ፤ ነገር ግን ያመንኩትን አውቃለሁና አላፍርበትም፤ የሰጠሁትንም አደራ እስከዚያ ቀን ድረስ ለመጠበቅ እንደሚችል እርግጠኛ ነኝ።