ነገር ግን እዚህ ድረስ መጥቼ በዐይኔ እስካየው ድረስ የተነገረኝን ሁሉ አላመንኩም ነበር፤ በጆሮዬ የሰማሁት በዐይኔ ያየሁትን እኩሌታ እንኳ አይሆንም፤ በእርግጥም ጥበብህና ሀብትህ በአገሬ ሳለሁ ከተነገረኝ በጣም ይበልጣል።
2 ዜና መዋዕል 9:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ግን መጥቼ በዓይኔ እስካየሁ ድረስ የነገሩኝን አላመንሁም፤ እነሆ፥ የጥበብህን ታላቅነት እኩሌታ አልነገሩኝም፤ ከሰማሁት ዝና ትበልጣለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ መጥቼ የነገሩኝን በዐይኔ እስካይ ድረስ አላመንሁም ነበር፤ በርግጥም የጥበብህ ታላቅነት እኩሌታው እንኳ አልተነገረኝም፤ እኔ ከሰማሁት ዝና እጅግ ይልቃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ እዚህ መጥቼ ሁሉን ነገር በዐይኔ እስካየሁ ድረስ የተነገረኝን ሁሉ አላመንኩም ነበር፤ ታዲያ በጆሮዬ የሰማሁት በዐይኔ ያየሁትን እኩሌታ እንኳ አልሆነም፤ በእርግጥም ጥበብህ ከተነገረኝ በጣም ይበልጣል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ግን መጥቼ በዐይኔ እስካየሁ ድረስ የነገሩኝን አላመንሁም፤ እነሆ፥ የጥበብህን ታላቅነት እኩሌታ አልነገሩኝም፤ በሀገሬ ከሰማሁትም ዝና ይልቅ ጨመርህልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ግን መጥቼ በዐይኔ እስካየሁ ድረስ የነገሩኝን አላመንሁም፤ እነሆ፥ የጥበብህን ታላቅነት እኵሌታ አልነገሩኝም፤ ከሰማሁት ዝና ትበልጣለህ። |
ነገር ግን እዚህ ድረስ መጥቼ በዐይኔ እስካየው ድረስ የተነገረኝን ሁሉ አላመንኩም ነበር፤ በጆሮዬ የሰማሁት በዐይኔ ያየሁትን እኩሌታ እንኳ አይሆንም፤ በእርግጥም ጥበብህና ሀብትህ በአገሬ ሳለሁ ከተነገረኝ በጣም ይበልጣል።
እርሱ ከሰዎች ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ ጥበበኛ ነበረ። ከኤዝራሐዊው ኤታን፥ የማሖል ልጆች ከሆኑት ከሄማን፥ ከካልኮልና ከዳርዓዕ የሚበልጥ ጥበበኛ ነበረ፤ ዝናውም ከፍ ብሎ በጐረቤት ሕዝቦች ሁሉ ዘንድ አስተጋባ።
ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ቢገለጥ ግን እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን፥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና።