Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 9:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ይሁን እንጂ እዚህ መጥቼ ሁሉን ነገር በዐይኔ እስካየሁ ድረስ የተነገረኝን ሁሉ አላመንኩም ነበር፤ ታዲያ በጆሮዬ የሰማሁት በዐይኔ ያየሁትን እኩሌታ እንኳ አልሆነም፤ በእርግጥም ጥበብህ ከተነገረኝ በጣም ይበልጣል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ይሁን እንጂ መጥቼ የነገሩኝን በዐይኔ እስካይ ድረስ አላመንሁም ነበር፤ በርግጥም የጥበብህ ታላቅነት እኩሌታው እንኳ አልተነገረኝም፤ እኔ ከሰማሁት ዝና እጅግ ይልቃል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እኔ ግን መጥቼ በዓይኔ እስካየሁ ድረስ የነገሩኝን አላመንሁም፤ እነሆ፥ የጥበብህን ታላቅነት እኩሌታ አልነገሩኝም፤ ከሰማሁት ዝና ትበልጣለህ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እኔ ግን መጥቼ በዐ​ይኔ እስ​ካ​የሁ ድረስ የነ​ገ​ሩ​ኝን አላ​መ​ን​ሁም፤ እነሆ፥ የጥ​በ​ብ​ህን ታላ​ቅ​ነት እኩ​ሌታ አል​ነ​ገ​ሩ​ኝም፤ በሀ​ገሬ ከሰ​ማ​ሁ​ትም ዝና ይልቅ ጨመ​ር​ህ​ልኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እኔ ግን መጥቼ በዐይኔ እስካየሁ ድረስ የነገሩኝን አላመንሁም፤ እነሆ፥ የጥበብህን ታላቅነት እኵሌታ አልነገሩኝም፤ ከሰማሁት ዝና ትበልጣለህ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 9:6
11 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን እዚህ ድረስ መጥቼ በዐይኔ እስካየው ድረስ የተነገረኝን ሁሉ አላመንኩም ነበር፤ በጆሮዬ የሰማሁት በዐይኔ ያየሁትን እኩሌታ እንኳ አይሆንም፤ በእርግጥም ጥበብህና ሀብትህ በአገሬ ሳለሁ ከተነገረኝ በጣም ይበልጣል።


እርሱ ከሰዎች ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ ጥበበኛ ነበረ፤ ከኤዝራሐዊው ኤታን፥ የማሖል ልጆች ከሆኑት ከሄማን፥ ከካልኮልና ከዳርዓዕ የሚበልጥ ጥበበኛ ነበረ፤ ዝናውም ከፍ ብሎ በጐረቤት ሕዝቦች ሁሉ ዘንድ አስተጋባ፤


በመላው ዓለም የሚገኙ ነገሥታት ስለ ሰሎሞን ጥበብ ሰምተው የእርሱን ጥበብ ያዳምጡ ዘንድ መልእክተኞቻቸውን ይልኩ ነበር።


ንጉሥ ሰሎሞንንም እንዲህ አለችው “ስለ አንተ ሥራና ስለ ጥበብህ ታላቅነት በአገሬ ሳለሁ የሰማሁት ሁሉ እውነት ነው!


ዘወትር በአንተ ፊት በመገኘት ጥበብ የተሞላበት ንግግርህን የሚሰሙ ባለሟሎችና አገልጋዮችህ እንዴት የታደሉ ናቸው!


በአንተ ለመከለል ወደ አንተ ለሚጠጉ በሰዎች ሁሉ ፊት የምትሰጠው ለሚፈሩህ ያዘጋጀኸው ደግነት ምንኛ ትልቅ ነው!


የምድሪቱም መልካምነትና ውበት ምንኛ አስደናቂ ይሆናል! በእርስዋ የሚገኘው እህልና የወይን ጠጅ ወጣት ወንዶችና ሴቶችን ያለመልማቸዋል።


ይሁን እንጂ መጽሐፍ፥ “የሰው ዐይን ያላየውን፥ የሰው ጆሮ ያልሰማውን፥ የሰው ልብ ያላሰበውን፥ እግዚአብሔር ለሚወዱት አዘጋጅቶአል” ይላል።


ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ወደፊት ምን እንደምንሆንም ገና አልታወቀም፤ ነገር ግን ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እውነተኛ መልኩን ስለምናይ እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos