ዕድሜህን ጨርሰህ ከአባቶችህ ጋር በምታንቀላፋበት ጊዜ፥ በእግርህ እንዲተካ ከአብራክህ የተከፈለ ዘር አስነሣልሃለሁ፤ መንግሥቱንም አጸናለሁ።
2 ዜና መዋዕል 9:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰሎሞንም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ በአባቱም በዳዊት ከተማ ተቀበረ፤ ልጁም ሮብዓም በእርሱ ፋንታ ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሰሎሞን ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ በአባቱ በዳዊት ከተማ ቀበሩት። ልጁም ሮብዓም በርሱ ፈንታ ነገሠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ ሞተ፤ በዳዊት ከተማም ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ሮብዓም ነገሠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሎሞንም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በአባቱም በዳዊት ከተማ ቀበሩት፤ ልጁም ሮብዓም በእርሱ ፋንታ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰሎሞንም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በአባቱም በዳዊት ከተማ ተቀበረ፤ ልጁም ሮብዓም በእርሱ ፋንታ ነገሠ። |
ዕድሜህን ጨርሰህ ከአባቶችህ ጋር በምታንቀላፋበት ጊዜ፥ በእግርህ እንዲተካ ከአብራክህ የተከፈለ ዘር አስነሣልሃለሁ፤ መንግሥቱንም አጸናለሁ።