ይህም ሁሉ ነጋዴዎች ከሚከፍሉት ቀረጥ፥ ከንግድ ከሚገኘው ትርፍ፥ እንዲሁም ከዐረብ ነገሥታትና ከእስራኤል ክፍላተ ሀገር አስተዳዳሪዎች ከሚገባለት ግብር ጋር ተጨማሪ ነበር።
2 ዜና መዋዕል 9:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነጋድራሶችና ነጋዴዎች የሚያመጡትን ወርቅ የሚጨምር አልነበረም፤ የዓረብም ነገሥታት ሁሉ የምድሩም ሹማምንት ወርቅና ብር ወደ ሰሎሞን ያመጡ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ከታላላቅና ከተራ ነጋዴዎች ከሚገባው ቀረጥ ሌላ ነበር። መላው የዐረብ ነገሥታትና አገረ ገዦች ለሰሎሞን ወርቅና ብር ያመጡለት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ነጋዴዎች ከሚከፍሉት ቀረጥ፥ እንዲሁም ከዐረብ ነገሥታትና ከእስራኤል ክፍላተ ሀገር አስተዳዳሪዎች ከሚገባለት ግብር ሌላ ተጨማሪ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነጋድራሶችና ነጋዴዎች ከሚያመጡት ሌላ የዓረብ ነገሥታት ሁሉ፥ የምድሩም ሹሞች ወደ ንጉሡ ሰሎሞን ወርቅና ብር ያመጡ ነበር መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዓረብም ነገሥታት ሁሉ የምድሩም ሹማምት ወርቅና ብር ወደ ሰሎሞን ያመጡ ነበር። |
ይህም ሁሉ ነጋዴዎች ከሚከፍሉት ቀረጥ፥ ከንግድ ከሚገኘው ትርፍ፥ እንዲሁም ከዐረብ ነገሥታትና ከእስራኤል ክፍላተ ሀገር አስተዳዳሪዎች ከሚገባለት ግብር ጋር ተጨማሪ ነበር።
ከፍልስጥኤማውያንም ለኢዮሣፍጥ እጅ መንሻና የብር ግብር ያመጡ ነበሩ፤ ዓረባውያንም ደግሞ ከመንጎቻቸው ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ በጎችና ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ ፍየሎች ያመጡለት ነበር።
ንጉሡም ሰሎሞን በጥፍጥፍ ወርቅ ሁለት መቶ አላባሽ አግሬ ጋሻ አሠራ፤ በአንዱም አላባሽ አግሬ ጋሻ ውስጥ የገባው ጥፍጥፍ ወርቅ ስድስት መቶ ሰቅል ነበረ።