2 ዜና መዋዕል 7:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰባት ቀንም መሠዊያውን ቀድሰው፥ ሰባት ቀንም በዓል አድርገው ነበርና በስምንተኛው ቀን የተቀደሰውን ጉባኤ አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሠዊያውን ለሰባት ቀን ስለ ቀደሱና የሰባት ቀን በዓል በተጨማሪ ስላከበሩ፣ በስምንተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አደረጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሠዊያውን ለእግዚአብሔር የተለየ በማድረግ ሥነ ሥርዓት ላይ ሰባት ቀን አሳለፉ፤ ሌላ ሰባት ቀን በዓሉን በማክበር ከሰነበቱ በኋላ በስምንተኛው ቀን የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት ተደርጎ የበዓሉ ፍጻሜ ሆነ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መሠዊያውንም ቀድሶ፥ ሰባት ቀን በዓል አድርጎ ነበርና በስምንተኛው ቀን የፍጻሜ በዓል አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰባት ቀንም መሠዊያውን ቀድሰው፥ ሰባት ቀንም በዓል አድርገው ነበርና በስምንተኛው ቀን የተቀደሰውን ጉባኤ አደረጉ። |
በዚያም በቤተ መቅደሱ ሰሎሞንና የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ሰባት ቀን ሙሉ የዳስ በዓል አክብረው ሰነበቱ፤ በስተ ሰሜን ከሐማት መተላለፊያ አንሥቶ በስተ ደቡብ እስከ ግብጽ ድንበር ድረስ ካለው ምድር ሁሉ የመጣው ሕዝብ እጅግ ብዙ ነበር።
ከካህናቱም እጅግ ብዙ ተቀድሰው ነበርና ጉባኤው ሁሉ እንደገና ሰባት ቀን በዓሉን ለማክበር ተማከሩ፤ በደስታም እንደገና ሰባት ቀን በዓሉን አከበሩ፤
በሰባተኛውም ወር በሃያ ሦስተኛውም ቀን ሕዝቡን ወደ ድንኳናቸው አሰናበተ፤ ጌታ ለዳዊትና ለሰሎሞን ለሕዝቡም ለእስራኤል ስላደረገው ቸርነት ደስ ብሎአቸው ሐሴትን እያደረጉ ሄዱ።
ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው ቀን ድረስ ዕዝራ ዕለት ዕለት የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ ያነብብ ነበር። በዓሉን ሰባት ቀን አከበሩ፤ በስምንተኛው ቀን በሕጉ መሠረት የተቀደሰ ጉባኤ ነበረ።
ሰባት ቀን ለጌታ በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን አቅርቡ፤ በስምንተኛውም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፥ ለጌታም በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን አቅርቡ፤ ዋና ጉባኤ ነው፤ የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት።