2 ዜና መዋዕል 4:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም በዮርዳኖስ ሜዳ በሱኮትና በጽሬዳ መካከል ባለው በሸክላው መሬት ላይ አስፈሰሰው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም እነዚህ ዕቃዎች በዮርዳኖስ ሸለቆ፣ በሱኮትና በጸሬዳ መካከል ባለው በሸክላ ዐፈር ቦታ ቀልጠው በሸክላ ቅርጽ ተሠርተው እንዲወጡ አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሰሎሞን እነዚህን ዕቃዎች ሁሉ ያሠራው በዮርዳኖስ ሸለቆ፥ በሱኮትና በጸሬዳ መካከል በሚገኘው በነሐስ ማቅለጫ ስፍራ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም በዮርዳኖስ ሜዳ በሱኮትና በሴድራ መካከል ባለው በወፍራሙ መሬት ውስጥ አቀለጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም በዮርዳኖስ ሜዳ በሱኮትና በጽሬዳ መካከል ባለው በወፍራሙ መሬት ውስጥ አስፈሰሰው። |