ሑራም የእያንዳንዳቸው ቁመት ስምንት ሜትር፥ የዙሪያ ስፋታቸው አምስት ሜትር ከሠላሳ ሳንቲ ሜትር ውስጡ ክፍት የሆነ አራት ጣት ውፍረት ካለው ነሐስ ሁለት ምሰሶዎችን ሠራ።
2 ዜና መዋዕል 4:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለቱን ዓምዶች፥ ጽዋዎቹንም፥ በዓምዶቹም ላይ የነበሩትን ሁለት ጉልላቶች፥ በዓምዶቹም ላይ የነበሩትን የጉልላቶች ሁለቱን ጽዋዎች የሚሸፍኑትን ሁለቱን መርበቦች ሠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለቱን አዕማድ፣ በአዕማዱ ጫፎች ላይ ያሉትን ሁለት ባለሳሕን ጕልላቶችን፤ በአዕማዱ ላይ ያሉትን ባለሳሕን ቅርጽ ሁለት ጕልላቶችን ያስጌጡትን ሁለት መረቦች፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለት ዐምዶችንና በሁለቱ ዐምዶች ላይ ጕልላቶችን፥ በዐምዶቹም ራሶች ላይ ያሉትን ጕልላቶች የሚሸፍኑ ሁለት መርበቦችን ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለቱን አዕማድ፥ ጽዋዎቹንም፥ በፃምዶቹምም ላይ የነበሩትን ሁለት ጕልላቶች፥ በዓምዶቹም ላይ የነበሩትን የጕልላቶች ሁለቱን ጽዋዎች የሚሸፍኑትን ሁለቱን መርበቦች ሠራ። |
ሑራም የእያንዳንዳቸው ቁመት ስምንት ሜትር፥ የዙሪያ ስፋታቸው አምስት ሜትር ከሠላሳ ሳንቲ ሜትር ውስጡ ክፍት የሆነ አራት ጣት ውፍረት ካለው ነሐስ ሁለት ምሰሶዎችን ሠራ።
ሁለቱ ምሰሶዎች፥ በምሰሶዎቹም ላይ የነበሩትን ማቶቶች የሚመስሉ ጉልላቶች፥ በምሰሶውም ላይ የነበሩትን ሁለቱን ጉልላቶች የሚሸፍኑት ሁለቱ መረቦች።
በዓምዶቹም ላይ የነበሩትን ሁለቱን ጉልላቶች እንዲሸፍኑ፥ ለእያንዳንዱ መረበብ በሁለት በሁለት ረድፍ ያሉ ሮማኖች፥ ለሁለቱ መርበቦች አራት መቶ ሮማኖች አደረገ።