La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 36:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢዮአቄምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ አምስት ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ በአምላኩም በጌታ ፊት ክፉ አደረገ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢዮአቄም በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ ዐምስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ። በአምላኩም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢዮአቄም በይሁዳ ላይ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ኻያ አምስት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ፤ እርሱም ኃጢአት በመሥራቱ አምላኩን እግዚአብሔርን አሳዘነ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኢዮ​አ​ቄ​ምም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ አም​ስት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ዘካራ የም​ት​ባል የኔ​ሬ​ያሳ ልጅ የራማ ሴት ነበ​ረች፤ አባ​ቶ​ቹም እን​ዳ​ደ​ረጉ በአ​ም​ላኩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ። 5 ‘ሀ’ በእ​ነ​ዚ​ያም ወራት የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ወደ​ዚያ ሀገር መጣና ሦስት ዓመት ተገ​ዛ​ለት። ከእ​ር​ሱም ከዳ። 5 ‘ለ’ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ን​ንና የሶ​ር​ያ​ው​ያ​ንን፥ የሞ​ዓ​ባ​ው​ያ​ን​ንና የአ​ሞ​ና​ው​ያ​ንን ልጆ​ችና የሰ​ማ​ር​ያን አደጋ ጣዮች ላከ​በት፤ ከዚ​ህም በኋላ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ በነ​ቢ​ያት እንደ ተነ​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ራቁ። 5 ‘ሐ’ ነገር ግን ምናሴ ስለ​ሠ​ራ​ቸው ኀጢ​አ​ቶ​ችና ኢዮ​አ​ቄም ስላ​ፈ​ሰ​ሰው ንጹሕ ደም፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም በን​ጹሕ ደም ስለ ሞላት ከፊቱ ይርቁ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በይ​ሁዳ ላይ ነበር። 5 ‘መ’ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሊያ​ጠ​ፋ​ቸው አል​ፈ​ለ​ገም ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢዮአቄምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ አምስት ዓመት ጕልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም አሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ በአምላኩም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ።

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 36:5
11 Referencias Cruzadas  

በይሁዳም ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን፥ እስከ ይሁዳ ንጉሥ እስከ ኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያስ ዐሥራ አንደኛው ዓመት ፍጻሜ፥ ኢየሩሳሌም እስከ ተማረከችበት እስከ አምስተኛው ወር ድረስ መጣ።


በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም መንግሥት መጀመሪያ ይህ ቃል ከጌታ ዘንድ መጣ።


በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን ከጌታ ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፦


እንዲህም ሆነ፤ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት ይህ ቃል ከጌታ ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጣ።


በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት የኔርያ ልጅ ባሮክ ኤርምያስ በቃል እየነገረው እነዚህን ቃሎች በመጽሐፍ በጻፋቸው ጊዜ፥ ነቢዩ ኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው።