2 ዜና መዋዕል 36:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአገሩም ሰዎች የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአክስን ወስደው በአባቱ ፋንታ በኢየሩሳሌም አነገሡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአገሩም ሰዎች የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአካዝን ወስደው በአባቱ ምትክ በኢየሩሳሌም አነገሡት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳ ሕዝብ የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአካዝን መርጠው በአባቱ እግር ተተክቶ በኢየሩሳሌም እንዲነግሥ አደረጉት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሀገሩም ሰዎች የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአክስን ወስደው በአባቱ ፋንታ በኢየሩሳሌም አነገሡት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአገሩም ሰዎች የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአክስን ወስደው በአባቱ ፋንታ በኢየሩሳሌም አነገሡት። |
በአባቱ በኢዮስያስ ፋንታ ስለ ነገሠው ከዚህም ስፍራ ስለ ወጣው ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ሰሎም ጌታ እንዲህ ይላልና፦ “ዳግመኛ ወደዚህ አይመለስም፥
“ጌታ አንተን በአንተም ላይ የምታነግሠውን ንጉሥ አንተና አባቶችህ ወደማታውቁት ሕዝብ ይወስዳችኋል። በዚያም ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ ሌሎች አማልክትን ታመልካለህ።