La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 35:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የእስራኤልም ንጉሥ ዳዊትና ልጁም ሰሎሞን እንደ ጻፉት በየሰሞናችሁና በየአባቶቻችሁ ቤቶች ራሳችሁን አዘጋጁ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በእስራኤል ንጉሥ በዳዊትና በልጁ በሰሎሞን በተጻፈው መመሪያ መሠረት፣ እንደየቤተ ሰባችሁ በክፍል በክፍላችሁ ራሳችሁን አዘጋጁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ንጉሥ ዳዊትና ልጁም ንጉሥ ሰሎሞን በሰጡአችሁ መመሪያ መሠረት በየጐሣችሁ በመመደብ በቤተ መቅደስ አገልግሎት ቦታ ቦታችሁን ያዙ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ዳዊት እንደ አዘዘ፥ ልጁም ሰሎ​ሞን እንደ አዘዘ በየ​ሰ​ሞ​ና​ች​ሁና በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ቤቶች ተዘ​ጋጁ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእስራኤልም ንጉሥ ዳዊትና ልጁም ሰሎሞን እንደ ጻፉት በየሰሞናችሁና በየአባቶቻችሁ ቤቶች ተዘጋጁ፤

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 35:4
5 Referencias Cruzadas  

የአሮንም ልጆች አመዳደብ ይህ ነው። የአሮን ልጆች ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር ነበሩ።


የጌታም ሰው ዳዊት እንዲህ አዝዞ ነበርና ካህናቱን እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሥርዓት በየአገልግሎታቸው ሰሞን ከፈላቸው፤ ሌዋውያንም እንደ ሥርዓታቸው እንዲያመሰግኑ፥ በካህናቱም ፊት እንዲያገለግሉ በየሰሞናቸው ከፈላቸው፤ ጠባቂዎችንም ደግሞ በየበሩ ሁሉ በየሰሞናቸው ከፈላቸው።