የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር ከወጡ ከአራት መቶ ሰማኒያ ዓመት በኋላ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፥ ዚፍ ተብሎ በሚጠራው በሁለተኛው ወር የጌታን ቤተ መቅደስ መሥራት ጀመረ።
2 ዜና መዋዕል 3:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤት ለመሥራት የጣለው መሠረት ይህ ነው፤ ርዝመቱም በዱሮው መለክያ መሠረት ስልሳ ክንድ፥ ወርዱም ሀያ ክንድ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰሎሞን ለአምላክ ቤተ መቅደስ ሕንጻ የጣለው መሠረት በቀድሞው ስፍር ልክ ርዝመቱ ስድሳ ክንድ፣ ወርዱም ሃያ ክንድ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሰሎሞን ያሠራው ቤተ መቅደስ ርዝመቱ ኻያ ሰባት ሜትር ሲሆን፥ ወርዱ ዘጠኝ ሜትር ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤት ይሠራ ዘንድ የጣለው መሠረት ይህ ነው፤ ርዝመቱም በዱሮው ስፍር ስድሳ ክንድ፥ ወርዱም ሃያ ክንድ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤት ይሠራ ዘንድ የጣለው መሠረት ይህ ነው፤ ርዝመቱም በዱሮው ስፍር ስድሳ ክንድ፥ ወርዱም ሃያ ክንድ ነበረ። |
የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር ከወጡ ከአራት መቶ ሰማኒያ ዓመት በኋላ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፥ ዚፍ ተብሎ በሚጠራው በሁለተኛው ወር የጌታን ቤተ መቅደስ መሥራት ጀመረ።
የመግቢያው ወርድ ዐሥር ክንድ ነበረ፥ የመግቢያው መቃኖች በዚህ ወገን አምስት ክንድ በዚያ ወገን ደግሞ አምስት ክንድ ነበሩ፤ ርዝመቱን አርባ ክንድ ወርዱን ደግሞ ሀያ ክንድ አድርጎ ለካ።