ባቢሎናውያን በቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበሩትን የነሐስ ዐምዶች፥ ባለ መንኰራኲር የዕቃ ማስቀመጫዎችና ከነሐስ የተሠራውን ታላቅ የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ ሰባበሩ፤ ነሐሱንም ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰዱት።
2 ዜና መዋዕል 3:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቤቱም ፊት ቁመታቸው ሠላሳ አምስት ክንድ የነበረውን ሁለቱን ዓምዶች ሠራ፥ በእያንዳንዳቸውም ላይ የነበረው ጉልላት አምስት ክንድ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቤተ መቅደሱም ፊት ለፊት በአንድነት ቁመቱ ሠላሳ ዐምስት ክንድ የሆነ፣ በእያንዳንዱም ላይ ዐምስት ክንድ ጕልላት ያለው ሁለት ዐምድ ሠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሰሎሞን የእያንዳንዱ ቁመት ዐሥራ አምስት ሜትር ተኩል የሆነ ሁለት ምሰሶዎችን ሠርቶ፥ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አቆማቸው፤ በእያንዳንዱም ምሰሶ ጫፍ ላይ ቁመታቸው ሁለት ሜትር ከኻያ ሳንቲ ሜትር የሆነ ሁለት ጉልላቶች ነበሩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቤቱም ፊት ቁመታቸው ሠላሳ አምስት ክንድ የነበረውን ሁለቱን ዐምዶች ሠራ፤ በእያንዳንዳቸውም ላይ የነበረው ጕልላት አምስት ክንድ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቤቱም ፊት ቁመታቸው ሠላሳ አምስት ክንድ የነበረውን ሁለቱን ዓምዶች ሠራ፤ በእያንዳንዳቸውም ላይ የነበረው ጕልላት አምስት ክንድ ነበረ። |
ባቢሎናውያን በቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበሩትን የነሐስ ዐምዶች፥ ባለ መንኰራኲር የዕቃ ማስቀመጫዎችና ከነሐስ የተሠራውን ታላቅ የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ ሰባበሩ፤ ነሐሱንም ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰዱት።