2 ዜና መዋዕል 29:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማቅረቡንም በፈጸሙ ጊዜ ንጉሡና ከእርሱ ጋር የነበሩ ሁሉ አጐነበሱ ሰገዱም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሥዋዕቱ ሁሉ ቀርቦ ካበቃ በኋላ፣ ንጉሡና ዐብረውት የነበሩት ሁሉ ተንበርክከው ሰገዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሥዋዕቱን የማቅረብ ሥራ በተፈጸመ ጊዜ ንጉሥ ሕዝቅያስና በዚያ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ተንበርክከው ለእግዚአብሔር ሰገዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማቅረቡንም በፈጸሙ ጊዜ ንጉሡ፥ ከእርሱም ጋር የነበሩ ሁሉ አጐነበሱ፤ ሰገዱም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማቅረቡንም በፈጸሙ ጊዜ ንጉሡና ከእርሱ ጋር የነበሩ ሁሉ አጎነበሱ፤ ሰገዱም። |
ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ፦ “አምላካችሁን ጌታን ባርኩ” አላቸው። ጉባኤውም ሁሉ የአባቶቻቸውን አምላክ ጌታን ባረኩ፥ ራሳቸውንም አዘንብለው ለጌታና ለንጉሡ ሰገዱ።
የእስራኤልም ልጆች ሁሉ እሳቱ ሲወርድ የጌታም ክብር በቤቱ ላይ ሲሆን ያዩ ነበር፤ በወለሉም ላይ በግምባራቸው ወደ ምድር ተደፍተው ሰገዱ እንዲህም ብለው ጌታን አመሰገኑ፦ “እርሱ መልካም ነውና፥ ጽኑ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና።”