የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅም ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፥ የጌታንም ቤት መዛግብትና የንጉሡን ቤት መዛግብት ወሰደ፤ ሁሉንም ነገር ወሰደ፤ ደግሞም ሰሎሞን የሠራቸውን የወርቁን ጋሻዎች ወሰደ።
2 ዜና መዋዕል 28:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አካዝም ከጌታ ቤት ከንጉሡና ከአለቆቹም ቤት እኩሌታውን ገፈፈ፥ ለአሦርም ንጉሥ ሰጠ፤ ነገር ግን እንዲህ ማድረጉ አንዳች አልጠቀመውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አካዝም ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ፣ ከቤተ መንግሥቱና ከመሳፍንቱ ዕቃዎች ዘርፎ ለአሦር ንጉሥ ሰጥቶት ነበር፤ ነገር ግን አልረዳውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ አካዝ ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ፥ ከቤተ መንግሥቱና ከሕዝቡ መሪዎች ዘንድ ብዙ ወርቅ ወስዶ ለንጉሠ ነገሥቱ መማለጃ አድርጎ ሰጠ፤ ይሁን እንጂ ይህን ማድረጉም አልጠቀመውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አካዝም ከእግዚአብሔር ቤት ከንጉሡና ከአለቆቹም ቤት የነበረውን ሁሉ ወሰደ፤ ለአሦርም ንጉሥ ሰጠ፥ ነገር ግን አስጨነቀው እንጂ አልረዳውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አካዝም ከእግዚአብሔር ቤት ከንጉሡና ከአለቆቹም ቤት እኵሌታውን ገፈፈ፤ ለአሦርም ንጉሥ ሰጠ፤ ነገር ግን አንዳች አልተጠቀመበትም። |
የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅም ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፥ የጌታንም ቤት መዛግብትና የንጉሡን ቤት መዛግብት ወሰደ፤ ሁሉንም ነገር ወሰደ፤ ደግሞም ሰሎሞን የሠራቸውን የወርቁን ጋሻዎች ወሰደ።
ኤፍሬምም ደዌውን፥ ይሁዳም ቁስሉን ባየ ጊዜ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፥ ወደ ታላቁም ንጉሥ መልእክተኛን ላከ፤ እርሱ ግን ሊፈውሳችሁ፥ ከቁስላችሁም ሊያድናችሁ አልቻለም።