2 ዜና መዋዕል 27:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮአታምም በአምላኩ በጌታ ፊት መንገዱን አቅንቶአልና በረታ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮአታም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት በታማኝነት ስለ ተመላለሰ፣ እየበረታ ሄደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአታም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት መንገዱን ስለ አቀና ገናና እየሆነ ሄደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአታምም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት መንገዱን አቅንቶአልና በረታ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአታምም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት መንገዱን አቅንቶአልና በረታ። |
ከአሞንም ልጆች ንጉሥ ጋር ተዋጋ አሸነፋአቸውም። በዚያም ዓመት የአሞን ልጆች መቶ መክሊት ብር፥ ዐሥር ሺህም የቆሬስ መስፈሪያ ስንዴ፥ ዐሥር ሺህም የቆሬስ መስፈሪያ ገብስ ሰጡት። እንዲሁም ደግሞ የአሞን ልጆች በሁለተኛውና በሦስተኛው ዓመት ተመሳሳ መጠን ያለውን ግብር ገበሩለት።