ነገር ግን በየኰረብቶች ላይ የነበሩትን የአሕዛብ መሠዊያዎችን አላስወገደም፤ ሕዝቡም መሥዋዕት ማቅረባቸውንና ዕጣን ማጠናቸውን እንደ ቀጠሉ ነበር፤ የቤተ መቅደሱን ሰሜናዊ ቅጽር በር ያሠራ ይኸው ኢዮአታም ነበር።
2 ዜና መዋዕል 27:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታን ቤት የላይኛውን በር ሠራ፥ በዖፌልም ቅጥር ላይ መጠነ ሰፊ ግንብ ገነባ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮአታም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የላይኛውን በር ሠራ፤ በዖፌልም በኩል ባለው ቅጥር ላይ፣ አያሌ የማሻሻል ተግባር አከናወነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአታም የቤተ መቅደሱን ሰሜናዊ በር እንደገና ሠራ፤ በተጨማሪም በኢየሩሳሌም በሚገኘው ዖፌል ተብሎ በሚጠራው ኰረብታማ ቦታ የከተማ ቅጽሮችን በመሥራት ብዙ ሥራ አከናውኖአል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርን ቤት የላይኛውን በር ሠራ፤ በዖፌልም ቅጥር ላይ ብዙ ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርን ቤት የላይኛውን በር ሠራ፤ በዖፌልም ቅጥር ላይ እጅግ ሠራ። |
ነገር ግን በየኰረብቶች ላይ የነበሩትን የአሕዛብ መሠዊያዎችን አላስወገደም፤ ሕዝቡም መሥዋዕት ማቅረባቸውንና ዕጣን ማጠናቸውን እንደ ቀጠሉ ነበር፤ የቤተ መቅደሱን ሰሜናዊ ቅጽር በር ያሠራ ይኸው ኢዮአታም ነበር።
የመቶ አለቆችንም፥ ከበርቴዎቹንም፥ የሕዝቡንም አለቆች፥ የአገሩንም ሕዝብ ሁሉ ወሰደ፥ ንጉሡንም ከጌታ ቤት ወስደው በላይኛው በር በኩል ወደ ንጉሡ ቤት መጡ፥ ንጉሡንም በመንግሥቱ ዙፋን ላይ አስቀመጡት።
ከዚህ በኋላ በዳዊት ከተማ በስተ ውጭው ከግዮን ምዕራብ በሸለቆው ውስጥ እስከ ዓሳ በር መግቢያ ድረስ ቅጥር ሠራ። በዖፌልም አዞረበት፥ እጅግም ከፍ አደረገው፤ በተመሸጉትም በይሁዳ ከተሞች ሁሉ የጭፍራ አለቆችን አኖረ።