La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 25:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አሜስያስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ አምስት ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ሀያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ዮዓዳን የተባለች የኢየሩሳሌም ሴት ነበረች።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አሜስያስ በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ ዐምስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ገዛ። እናቱም ዮዓዳን የተባለች የኢየሩሳሌም ሴት ነበረች።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አሜስያስ ዕድሜው ኻያ አምስት ዓመት ሲሆን ነገሠ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ኻያ ዘጠኝ ዓመት ገዛ፤ እናቱ ይሆዓዲን ተብላ የምትጠራ የኢየሩሳሌም ተወላጅ ነበረች፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አሜ​ስ​ያ​ስም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ አም​ስት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ፤ እናቱ ኢዮ​ዓ​ዲን የተ​ባ​ለች የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሴት ነበ​ረች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አሜስያስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ አምስት ዓመት ጕልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሀያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ዮዓዳን የተባለች የኢየሩሳሌም ሴት ነበረች።

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 25:1
2 Referencias Cruzadas  

የልጆቹና በእርሱ ላይ የተደረገው ነገር የጌታንም ቤት ማደሱ፥ እነሆ፥ በነገሥታቱ መጽሐፍ ተጽፎአል። ልጁም አሜስያስ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።