2 ዜና መዋዕል 24:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አለቆቹና ሕዝቡም ሁሉ ደስ ብሎአቸው ግብሩን አመጡ፥ እስኪሞላም ድረስ በሣጥኑ ውስጥ ጣሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሹማምቱ ሁሉ፣ ሕዝቡም ሁሉ ግብሩን በደስታ አመጡ፤ እስኪሞላም ድረስ በሣጥኑ ውስጥ ጨመሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ሕዝቡንና መሪዎቹን ሁሉ ደስ ስላሰኛቸው ገንዘብ በማምጣት ሣጥኑን ሞሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አለቆቹና ሕዝቡም ሁሉ ሰጡ፤ እስኪሞላም ድረስ በሣጥኑ ውስጥ አስገቡት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለቆቹና ሕዝቡም ሁሉ ደስ ብሎአቸው አቀረቡት፤ እስኪሞላም ድረስ በሣጥኑ ውስጥ ጣሉት። |
ሣጥኑም በሌዋውያን እጅ ወደ ንጉሡ ሹማምንት በመጣ ጊዜ፥ ብዙ ገንዘብም እንዳለበት ባየ ጊዜ፥ የንጉሡ ጸሐፊና የታላቁ ካህን ሹም እየመጡ ብሩን ከሣጥኑ ውስጥ ያወጡ ነበር፥ ሣጥኑንም ደግሞ ወደ ስፍራው ይመልሱት ነበር። እንዲህም በየቀኑ ያደርጉ ነበር፥ ብዙም ገንዘብ አከማቹ።
ጽድቅን የሚያደርገውን፥ በመንገዶችህም የሚያስቡህን ትገናኛቸዋለህ። እኛ ኃጢአት ሠራን፤ እነሆ፥ አንተ ተቈጥተህ ነበር፤ ፊትህን ስለሰወርክብን እኛ ተሳሳትን።